Get Mystery Box with random crypto!

' ባይተዋር ሌሊቶች ' መጽሐፍ ለንባብ በቃ ! ከመፅሀፉ የወደድኩትን እነሆ #ርዕስ:- #ሁ | ልብወለድ Ethio_Fiction

" ባይተዋር ሌሊቶች "
መጽሐፍ ለንባብ በቃ !

ከመፅሀፉ የወደድኩትን እነሆ

#ርዕስ:- #ሁለት_አንድ_ምስል

እሳት እየሞቁ
ዝምታ እየሳቁ
ወይን እያጣጣሙ
ትዝታ እየሰሙ…
በነገር መብሰልሰል፣
ጉርድ ጨረቃ ፊት
ያልሽኝን መመሰል…

ልንገርሽ… ልንገርሽ…
አንቺ የሌት ብርሃን፤ አንቺ የሌት ባለቤት፣
ግማሽ መሆንሽን የነገረሽ የለም
ሙሉ ነሽ ባንቺ ቤት፡፡

ልንገርሽ… ልንገርሽ…
እሳት ዳር ተቀምጠው
ትዝታን መሞቁ፣
ብርድ ልብስ አስጥተው
ፀሐይ መጠበቁ፣
በሚወርድ ዶፍ መሃል
ከማይደርቅ ብሶት፤ ቃል ብይን መጭመቁ…

ልንገርሽ… ልንገርሽ…
አንቺ ግማሽ ብርሃን
የአምና ባለቤት
ልቤን እንደሞላሽ
የነገረሽ የለም ሽርፍ ነሽ ባንቺ ቤት::