Get Mystery Box with random crypto!

' ሽማግሌ ከእንቅልፍ ሌላ ምን አለዉ ልጄ ለሊት ዶፍ ጣለብኝና በርዶኝ እንቅልፍ አልወስድ አለኝ አ | ልብወለድ Ethio_Fiction

" ሽማግሌ ከእንቅልፍ ሌላ ምን አለዉ ልጄ ለሊት ዶፍ ጣለብኝና በርዶኝ እንቅልፍ አልወስድ አለኝ አሁን ነዉ የጠዋቱ ፀሀይ ስታገኘኝ... "

ንግግራቸዉን አቋርጠዉ ለመቀመጥ ሙከራ ሲያደርጉ መጪዉን የክረምት ወራት አስባ ሎዛ ነፍሷ እየተጨነቀ አዛዉንቱን ተመለከተቻቸዉ
አዛዉንቱ ግዙፍ ናቸዉ ወይም ሁልጊዜ ልብስ ደርበዉ ስለምትመለከታቸዉ ይሁን ብቻ ኮስማና ሆነዉ አይታዩዋትም ፡፡

ከተጨራመተዉ ቆዳቸዉ ስር ግንባራቸዉ ላይ የተጋደመዉ መስመር የተጓዙትን ህይወት፤ የረገጡትን መንገድ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ወደታች የተንጠለጠሉ ጉንጮቻቸዉን ስትመለከት እድሜያቸዉ ከ80-85 ሊሆን እንደሚችል ትገምታለች፡፡

ሁሌም የሚያብጡት አይኖቻቸዉ ዉስጥ የምታነበዉ ባይተዋርነት ያሳዝናታል፡፡ትዉዉቅ አድርጋ ልግስናዋን ማሳየት ከጀመረች አንድ አመት ቢያልፍም ተጠግታ ታሪካቸዉን ጠይቃ አታዉቅም የምታዉቀዉ ብቸኝነታቸዉን ብቻ ነዉ፡፡ "

ከመጽሐፉ የተወሰደ ::

ስርቅታ
በሰራዊት ተወልደ
የመጀመርያ ዕትም

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited