'..........ግጥም ላንብብላችሁ አለ ?! ' ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ተፈቀደለት። ግጥሞቹ | ልብወለድ Ethio_Fiction
"..........ግጥም ላንብብላችሁ አለ ?! " ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ተፈቀደለት።
ግጥሞቹ በየሰው እጅ ነው የሚገኙት ከጻፈ በኋላ የትም ይጥለዋል ። ለነገሩ የግጥም ሐሣብ ሲመጣለት ዛር እንዳለበት ያደርገዋል... ያጣድፈዋል።
" አስዬ ጨብራሪት መጣች ፣ አስዬ ጨብራሪት መጣች ፣ አስዬ ጨብራሪት መጣችብኝ … " ብሎ ይቁነጠነጣል ።
አስዬ ጨብራሪት የምታስፅፈው ዛር ናት ። ይህች ዛር ከመጣች አሁኑኑ ነው የምታስብለው ። በዚህ ጊዜ አጠገቡ ካሉ ሰዎች መካከል (ለምሣሌ ስንዱ) እስኪርብቶ አንስታ የሚለውን ትገለብጣለች ። አምስት …… ስድስት ወይም ሰባት ገጽ ሊሆን ይችላል።
" በቃሉ ነው የሚያወጣቸው " ሲባል ሰምቻለው ያልተጻፉ ግጥሞቹን ። ከተጻፈ በኋላ አይሰርዝም አይደልዝም ።
ከዛ "አንብቢልኝ " ይላል ። ታነባለች " ሸላይ ናት " ይላል በቃ ። ከእነዚህ ግጥሞች አንዱን አንብቦልን ሲጨርስ አስተያየት ጠየቀን ። እኔም የሚደነቀውን አድንቄ " ...ግን ከመጠን በላይ ረዥም ነው " አልኩት ። ፈጣን መልስ ሰጠኝ ።
" አንተ የበልግ ካፊያ ከሆንክ እኔ የሐምሌ ወጀብ እንዳልሆን ልትከለክለኝ አይገባም " አለኝ።
ቀደም ሲል አጫጭር ግጥሞች አቅርቤ ስለነበር ነው ። ግጥሞቼ በበልግ ካፊያ የመሰላቸው ።
" ጋሽ ስብሐት እንዴት አየሃት? " ጠየቀ።
" አልሰማኋትም .... " አለው ስብሐት ።
" አትኩረህ እያየኸኝ አልነበር ? "
" ..........መጀመሪያ ልሰማህ ጓጉቼ ነበር ። ቆይቶ ግን የግጥሙ ርዝመት ይሁን የቋንቋው ክብደት አላውቅም እኔና አንተን ለመለያየት ምክንያት ሆነን ። እናም አየሰማሁህ ጺምህን ሳይ ፣ ፊትህን ሳይ በስዕል የማውቀው የራሺያው ዶስቶቪስኪን መሰልከኝ ። አዬ መመሳሰል ብዬ ስገረም ስገረም ግጥምህን ጨረስከው አንድ ቀን ትደግምልኛለህ! " አለው።
※ እንዳለጌታ ከበደ በ2006 ከጻፈውና ካሳተመው ማዕቀብ መጽሐፍ የተቀነጨበ ።
#share -----> @ethio_fiction
#comment ---> @Cr7_reunited