Get Mystery Box with random crypto!

...ዶ/ር ኬይም ጌንት፤ (የናዚ ጀርመን ዘረኞች ከ6 ሚልየን በላይ አይሁዳውያን ሲገድሉ በተዓምር | ልብወለድ Ethio_Fiction

...ዶ/ር ኬይም ጌንት፤ (የናዚ ጀርመን ዘረኞች ከ6 ሚልየን በላይ አይሁዳውያን ሲገድሉ በተዓምር የተረፈ እስራኤላዊ የስነ አዕምሮ ስፔሻሊስት ነው።)

እርሱ እንዲህ አለ :-

"ሕይወቴ በአጋጣሚ ነው የተረፈው። ሚሊየኖች ሲገደሉ በአይኖቼ ተመልክቻለሁ።  ትምህርት ብቻውን ጠቃሚ እንዳልሆነም አይቻለሁ።

የተማሩ ኢንጂነሮች የጅምላ ግድያውን አዳራሽ ገነቡ::

የተማሩ ዶክተሮች ህጻናትን በመርዝ ገደሉ::

እመጫትና እናቶች በተማሩ ነርሶች ተገደሉ።

ሴቶችና ልጆች በኮሌጅ ምሩቃንና መምህራን ግንባራቸው በጥይት እየተመታ ሕይወታቸው እንደዋዛ አለፈ።

ታድያ ይህንን ሁሉ በተማሩ ሰዎች ሲፈጸም አይቼ፤ ትምህርት ብቻውን ጠቃሚ እንዳልሆነ ተገነዘብኩ።

... ....
ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ ሰብዓዊነትን ጭምር እንዲያስተምሩ እጠይቃለሁ። እርግጥ ነው ማንበብ፣ መጻፍና የሒሳብ እውቀት አስፈላጊና ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ።
ነገር ግን ልጆችን የቀለም ትምህርት ብቻ ሳይሆን
#ሰብዓዊነትንም ጭምር ማስተማር ግዴታችን ነው። "

የተወደዳችሁ የቻናሉ ቤተሰቦች
በዚህ ጉዳይ ዙርያ ምን ሃሳብ አላችሁ? በመወያያ ቡድኑ ላይ ሃሳባችሁን አስፍሩልን!

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited