" ... እዚህ አዲሳባ ውስጥ አንዳንድ ቦታ እንጀራ በቢላ ሲቆረስ እናያለን። ይኼ በቢላ እንጀራ የመቁረስ ባህል የጀመረው ማን ነው ? ለምን ጀመሩ ?
እንጀራን በቢላ መቁረስ እንጀራን ወደ ዳቦ ለማውረድ መጣር እንደሆነ አልተረዱትም?
የእኛ ትልቁ ችግራችን እውር ኮፒ አድራጊዎች መሆናችን ነው ። ፈረንጅ ዳቦ ሲቆርስ አይተን ከዛ በጭፍን ያለ ጥየቃ ያለትንታኔ ተበደርን ። የዚህ ችግር መነሻው በራሳችን ማመን አለመቻላችን ነው ። በራሱ የማያምን ሕዝብ ወደ ባርነት የሚጓዝ ነው።
ለመሆኑ እንጀራ ለመቁረስ እጅ አነሳትና ነው ቢላ የመጣባት ? በእንግሊዘኛ ኦቨርኪል (overkill) ይባላል። ዝንብ ለመግደል ታንክ ስታወጣ ማለት ነው ።
እንጀራ ቢደርቅ እንኳን አይፈነክትም :: እንጀራ ጥፊ እንኳን አይሆንም :: ምኑ ሰይፍ ያስመዝዛል?
ግን እንጀራ አገር ያቆማል ...”
#ምንጭ
እቴሜቴ ሎሚሽታ ----አዳም ረታ
Share :- @ethio_fiction
Inbox :- @Cr7_reunited