Get Mystery Box with random crypto!

የአመፃ ልጅ (Born a crime) ቋንቋን በተመለከተ እየተሻኮታችሁ ላላችሁ ሁሉ ከትሬቨር ኖህ | ልብወለድ Ethio_Fiction

የአመፃ ልጅ (Born a crime)

ቋንቋን በተመለከተ እየተሻኮታችሁ ላላችሁ ሁሉ ከትሬቨር ኖህ "Born a Crime" መፅሐፍ ላይ ከተተረጎመው "የአመፃ ልጅ" መፅሃፍ "ምትሃተኛው" ምዕራፍ ላይ ይሄንን ቅንጭብ ታነብቡ ዘንድ ጋብዤአችኋለሁ።

..... .....
"እኔም ልክ እንደ እናቴ ብዙ ቋንቋዎችን መናገር ቻልሁ። ንግግራችሁን አስመስዬ ለራሳችሁ መልሼ በማውራት የተካንሁ ነበርሁ። አንዳንድ ጊዜ በጎዳና ላይ ስሄድ ሰዎች በጥርጣሬ አይን እየተመለከቱኝ "ከየት ነው የመጣኸው?" በማለት ሲጠይቁኝ ባናገሩኝ ቋንቋና የአነጋገር ዘዬ ስመልስላቸው ፊታቸው ላይ የግርምት ቅፅበት እየታየና ጥርጣሬያቸው እየተገፈፈ "ይገርማል! ጥሩ ነው። እንግዳ መስለኸን ነው። እንደዚያ ከሆነ ጥሩ።" ብለው ይመልሱልኛል።

..... .....
ቋንቋ እድሜ ልኬን የተጠቀምኩበት መገልገያዬ ነበር። አንድ ቀን ወጣት ሳለሁ መንገድ ላይ ብቻዬን እየሄድሁ የዙሉ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች በቡድን ሆነው እየተከተሉኝ አጠገቤ ሲደርሱ እንዴት አድርገው እንደሚጥሉኝ ሲያወሩ ሰማኋቸው። "ይሄንን ነጫጭባ ሃንግ እንሥራው። “አንተ በግራ በኩል ሂድ። እኔ ከኋላ ሄድበታለሁ” ሲባባሉ ስሰማ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። መሮጥ አቃተኝ። ድንገት በፍጥነት ወደ ኋላ ዞሬ በዙሉኛ "ስሙ ልጆች ለምን አብረን ሌላ ሰው ማጅራት አንመታም? እኔ ዝግጁ ነኝ። እናድርገው!” አልኋቸው።
ልጆቹ ንግግሬን ሲሰሙ ለጥቂት ጊዜ ክው ብለው ከደነገጡ በኋላ መሳቅ ጀመሩ "ኧረ ጓደኛችን ይቅርታ! ሌላ ነገር መስለኸን ነው። ካንተ ምንም ለመውሰድ አስበን አይደለም። እኛ ለመስረቅ የምንፈልገው ከነጮች ላይ ነው። መልካም ቀን ይሁንልህ ወዳጃችን!" ብለው ጥለውኝ ሄዱ። አንድ ጎሳ መሆናችንን ሳይረዱ በፊት ደብድበው ሊዘርፉኝ ነበር። ይሁን እንጂ ሰላም አወረድን። ይሄንን የመሳሰሉ ገጠመኞች የምናገረው ቋንቋ ከቆዳ ቀለሜ በበለጠ ሰዎች ስለ እኔ የሚኖራቸውን እይታ የሚበይን መሆኑን እንድገነዘብ አድርገውኛል።

.... ....
በጠቅላላው እንደ እስስት ነበርሁ ማለት ይቻላል። የቆዳ ቀለሜን ሳልቀይር ቋንቋን ተጠቅሜ እናንተ ስለእኔ ቆዳ ቀለም ያላችሁን አመለካከት መቀየር እችላለሁ። በዙሉኛ ካናገራችሁኝ በዙሉኛ እመልስላችኋለሁ። በፅዋናኛ ካናገራችሁኝ በፅዋናኛ እመልስላችኋለሁ። ምናልባት በመልክ ላልመስላችሁ እችል ይሆናል የእናንተን ቋንቋ መናገር ከቻልሁ ግን እናንተን እሆናለሁ።".......

.... ....
ለማንኛውም አስራ አንድ የሥራ ቋንቋ ካላት ደቡብ አፍሪቃ ብዙ ትምህርት እንማራለንና የትሬቨር ኖህን "የአመፃ ልጅ" ከመፅሐፍ መደብር ብቅ ብለው ይሸምቱና ያነቡት ዘንድ ጋበዝንዎ።

#share -----> @ethio_fiction

#comment ---> @Cr7_reunited