Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.97K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 148

2022-05-16 14:17:46
የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ

ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል።

የቢሮው ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው ትሕነግ የጥፋት መንገድ ተጋሪዎች የአማራን ሕዝብ አንድነት ለመሸርሸር በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን የተለያዩ አጀንዳዎችን እየዘረጉ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው የሽብር ቡድኑ አሁንም ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው ብለዋል።

የጥፋት ኃይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
71.9K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 12:35:37
በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ እና በቅርቡ በምስራቅ ወለጋ፣ ጉቶ ጊዳ ወረዳ፣ አለልቱ ቀበሌ ወደሚገኘው መኖሪያ ስፍራቸው ለተመለሱ 800 ግለሰቦች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) አስታውቋል

ድጋፍ ከተደረጉት ቁሳቁሶች መካከል ሶላር የእጅ ባትሪዎች ፣ ጀሪካኖች ፣ የማዕድ ቤት እቃዎች ፣ ምንጣፎች ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መጠለያ እንደሚገኙበት ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
66.0K views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 12:35:34
ETHIO FITNESS & NUTRITION (EFN ) አዳማ

በአጭር ጊዜ የሰውነታችንን ጡንቻ በፍጥነት ለማሳደግ ፣ የተስተካከለ አቋም ለማግኘት እና የሰውነት ክብደት መጨመሪያ እና መቀነሻ ፕሮቲን ፓውደር።

PLATINUM MASS ( 1KG)
WHEY CORE ( 908G)
MONOHYDRATE CRATINE ( 300G)
WHEY CORE ( 2.27KG)

Adress : አዳማ ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

Call +251966113766 ወይም በነፃ ስልክ መስመር ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን 9369

Inbox @ETHIO_FITNESS_NUTRITION

Join https://t.me/+UsMPjkAqaNVxN4Sl
64.2K views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 10:16:23 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሶማሊያን ለቀጣይ 4 ዓመታት ለመምራት አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ዳግም ከተመረጡት ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ጋር በጋራ ቀጣናዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ በድጋሚ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እወዳለሁ። የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንደምንሠራ እምነቴ ነው።"ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
66.4K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 20:18:10
በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸውን የገለፀው የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ነው፡፡

ከእነዚህ መካከል 10 የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች ከክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክክር ጉባኤ በኋላ ወደስራ የገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬን በጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ እንዲሁም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ 19 ሚሊየን 806 ሺህ 957 ከ80 ዶላር ማግኘት መቻሉም ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
29.8K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 13:45:26 ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለጸ

በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።የነዚህ ውጥረቶች መባባስና ይህንንም የሚያጋግሉ ትርክቶች በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል ብሏል ኢሰመኮ በዛሬው ዕለት ግንቦት 7፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ።

በተለይም አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ ሌላ ጦርነትም ሆነ ግጭት መሸከም እንደማትችል አፅንኦት ሰጥቷል።ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ ግሽበት ፣ የመሠረታዊ አቅርቦቶች እጥረትና ከሰሜን ኢትዮጵያ ሰፊ አካባቢዎች የሚደረጉ የምርት እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸው፣ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ሰብዓዊ ፍላጎቶችም የሃገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በእጅጉ ጎድተውታል ብሏል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ቀጣይ ግጭት እና ጦርነት የሚያስከፍለው በዋጋ የማይገመት ነው ያለው መግለጫው ሲቪል ህዝቦችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ እና ተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ ህግ ጥሰቶችን እንደሚያስከትልም አጽንኦት ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ለአስራ ስምንት ወራት የዘለቀው ጦርነት መቋጫ ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋን ዘርቶ የነበረ ቢሆንም ከሰሞኑ ዳግም ጦርነት ይከሰት ይሆን የሚሉ ፍንጮች ጥያቄ ፈጥረዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
10.0K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 13:45:25
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
9.8K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 18:00:28 ወንድሜ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እንኳን ደስ አለህ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የአንኳን ደስ ያለዎ መልእክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ "በሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በሳል አመራር በሀገሪቱ ዕድገት እና ብልጽግና እንዲመጣ ልባዊ ምኞቴ ነው" ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
22.9K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 11:49:52 አሸባሪው የህወሓት ቡድን አሁንም በአማራ እና አፋር ክልሎች በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች አለመውጣቱን መንግስት አስታወቀ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች እንደወጣ ቢያወራም አሁንም በአማራ ክልል በወረራ ከያዛቸው አዲአርቃይ፣ ጸለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎች እንዲሁም ከአፋር ክልል ደግሞ በራህሌ፣ ኮኖቫ፣ አብአላ፣ መጋሌ ወረዳዎች አልወጣም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ የሰብዓዊ እርዳታ እና ሰሜኑን የኢትዮጵያን ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የክልሉን ነዋሪዎች ለመታደግ ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔን ተከትሎ በየብስ እና በአየር ትራንስፖርት የሚጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል፡፡

የእርዳታ ፍሰቱንም የተሳለጠ ለማድረግ መንግስት ከእረጅ ድርጅቶች የሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን መፍታቱንም ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንትም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 165 ያህል የእርዳታ እህል የጫኑ ተሸከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸው በመግለጫው ተነስቷል፡፡

መንግስት አቅም በፈቀደ መጠን የእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ማቅረብ የሚችሉትን እርዳታ እንዲያቀርቡ ያላሰለሰ ጥረት ቢያደርግም÷ በአንጻሩ የትግራይ ወራሪ ኃይል የእርዳታ ማጓጓዝ ስራው እንዳይሳለጥ እንቅፋት እየሆነ ነው ብለዋል ዶክተር ለገሰ በመግለጫቸው፡፡

የእርዳታ እህል ለማሳለጥ ሲባል ከትግራይ ወጥተናል በሚል የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር የሚረጩት ወሬም መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
25.3K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 11:44:54
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል ብሎ የተጠረጠራቸውን የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ 4 አባላቱን አገደ

በፓርቲው የሥራ ኃላፊዎችና በአባላቱ ላይ እግድ የጣለው የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነው፡፡ግለሰቦቹ የሳምንት ሥራ መከታተያ ቅፅ በሚል ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው ግንቦት 2፣ 2014 በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የዋትስ አፕ ግሩፕ ላይ በመላክ ተጠናክረው መታገዳቸው ሸገር ከፓርቲው ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ከትናንት በስትያ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ሰነዱ ፍፁም ስህተት እና የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሂደት ዲሞክራሲያዊነትን የሚያቀጭጭ ብሎታል በውሳኔው፡፡በመሆኑም ሰነዱን አዘጋጅተዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 የፓርቲው አባላት በሰነዱ ላይ ያላቸውን ተሳትፎና የህግ ጥሰታቸው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለፓርቲው ህገ ደንብ ትርጉምና ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተመርቷል ተብሏል፡፡

ጉዳዩ በኮሚቴው ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስም ፡-

• የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ
• የፋይናንስ መምሪያ ሀላፊው አቶ አንድነት ሽፈራሁ
• የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደና
• አባል የሆኑት አቶ ኢዮብ መሳፍንት ከሀላፊነታቸው ለጊዜው እንዲታገዱ መወሰኑን ሸገር ራዲዮ ዘግቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
24.5K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ