Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 247.29K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-18 12:22:08
የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ

መሰረታቸውን በዉጪ ያደረጉ ባለሃብቶች በችርቻሮ እና በጅምላ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አስታውቀዋል።

ከጅምላ ንግድ ጋር ተያይዞ ከማዳበሪያና ከነዳጅ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል በዚህም በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ነዉ የተፈቀደው ።

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች አሁን ደግሞ ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
19.7K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 12:22:06
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://t.me/Poppycarmarket

0911248768   ይደውሉልን
19.2K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 12:21:56
➨ በኢትዮጵያ ትልቁን የአክሲዮን ትርፍ ክፍፍል ያስመዘገበው የአያት አክሲዮን ሽያጭ ሊጠናቀቅ  ጥቂት እጣዎች ቀሩት!!

አያት አክሲዮን ማህበር በ 2015 ዓ.ም 51.3% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍሏል

በቀላሉ
የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 513,000 ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር

ዝቅተኛ የአክሲዮን መጠን 2500 ጠቅላላ ዋጋ 250,000ብር

ቅድመ ክፍያ 112,500 ብር ቀሪ ክፍያ  በ 3 ዓመት የሚከፈል በየዓመቱ 50,000ብር

ከፍ ያለ የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ዳጎስ ያለ የአክሲዮን ትርፍ ያግኙ

ሽያጭ ከመጠናቀቁ በፊት ዛሬውኑ እርሶም የራስዎን ድርሻ ይውሠዱ

የሽያጭ ባለሙያዎቻችንን ለማግኘት (whatsapp/ telegram/direct)
  0904272788
18.3K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 14:48:20
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል

ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።

ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።

" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።

በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
38.7K views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 13:34:02
ዱባይ በጎርፍ ተጥለቀለቀች

በዱባይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች።

ጎርፉን ተከትሎ የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያን ጨምሮ የከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ከባድ ጎርፍ እያስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ከዚህ ቀደም በርከታ በረራዎችን ሲያስተናግድ በነበረው የዱባይ አየር መንገድ በረራዎች ተስተጓጉለዋል።

ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ በኦማን ተከስቶ 18 ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በባህሬን ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
39.5K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 11:36:13 አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ኢራን ላይ ማዕቀብ ለመጣል ዝግጅት ጀመሩ

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኅብረት፤ እስራኤል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተሰናዱ ነው።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ጃኔት የለን “በሚቀጥሉት ቀናት” እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ደግሞ ኅብረቱ ማዕቅብ ለመጣል እየሠራ መሆኑን ገልጠዋል።እስራኤል አጋሮቿ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።

የተባበሩት መንግሥታት የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ የጣለው ማዕቀብ ባለፈው ጥቅምት ጊዜው አብቅቷል።እኒህ ማዕቀቦች የሚጣሉት የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመግታት ነው የሚሉ ሐሳቦች ከፖለቲካ ተንታተኖች ዘንድ ይሰማሉ።አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ኢራን ላይ የተለያዩ ማዕቀቦች ከዚህ ቀደም መጣላቸው አይዘነጋም።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ሄርዚ ሀሌቪ ባለፈው ሰኞ በሰጡት አስተያየት ኢራን ያደረሰችው ጥቃት ምላሽ ሳያገኝ አያልፍም የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ባደረሰችበት ወቅት 300 ሚሳዔሎችና ድሮኖች ከራሷ ክልል፣ ከኢራቅ፣ ሶሪያ እና የመን አስወንጭፋለች።አብዛኛዎቹ ሚሳዔሎች እና ድሮኖች በእስራኤል እና አጋሮቿ ዒላማቸውን ሳይመቱ እንዲከሽፉ ተደርገዋል።ቴህራን እንዳለችው ጥቃቱን የሰነዘረችው እስራኤል፤ ሶሪያ በሚገኘው ቆንስላዋ ላይ ጥቃት አድርሳ 13 ሰዎችን ለገደለችበት ጥቃት አፀፋውን ለመመለስ ነው።

እስራኤል ለደረሰባት ጥቃት እስካሁን ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠችም። በምትኩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢራንን ለማሽመድመድ እየሠራች ትገኛለች።እስራኤል 30 የሚሆኑ አጋር ሀገሮች የኢራን የሚሳዔል ፕሮገራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።አልፎም እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኢስላሚክ ሪቮሎሺናሪ ጋርድ ኮር የተባለው የኢራን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ኃይል ሽብርተኛ ተብሎ እንዲፈረጅ ጠይቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ቡድኑን ሽብርተኛ ብትልም ዩኬ ይህን ከማድረግ ተቆጥባለች።

ማክሰኞ ዕለት ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትር የለን “በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንደምንጥል ይጠበቃል” ብለዋል።ሚኒስትሯ አክለው ኢራን ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ “ምናልባት የምናየው ይሆናል” ካሉ በኋላ “ኢራንም አሁንም በግልፅ ነዳጅ እየሸጠች ነው፤ ስለዚህ ጉዳይ የምናደርገው ነገር ይኖራል” ሲሉ ማዕቀቡ ምን ላይ እንደሚያተኩር ጠቁመዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
37.5K views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:14:07 ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

የክልሉ መንግሥት ፥ " ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ከሷል።

" ህወሓት የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል " ሲል አስታውሷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ህወሓትን " የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት " እንደሆነ ገልጾ " ባለፉት 3 ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል " ብሏል።

" የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ገልጿል።

" ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው ፦
- የራያ አላማጣ፣
- ራያ ባላ፣
- ኦፍላ፣
- ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች  ናቸው " ብሏል።

" ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ህወሓት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት በኃላ አካባቢዎቹ በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት እንደቻሉ " የአማራ ክልል መንግሥት ገልጿል።

በኃላም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ፤ ህወሓት ግን ስምምነቱን በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም እንደቆየ አመላክቷል።

" አሁንም እየፈጸመ ይገኛል " ብሏል።

የአማራ ክልል መንግሥት ፥ ህወሓት ደም አፋሳሽ የሆነ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲያከብር አሳስቧል።

" በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ " ሲል ጠይቋል።

" ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግናረ ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@Esat_tv1
@Esat_tv1
35.0K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:14:03
32.5K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 09:54:23
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
31.7K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 09:54:16
Niya Online payment

የተለያዩ እንደ SAT እና USMLE ያሉ የውጭ ፈተናዎችን ክፍያ ለመፈጸም ለ Scholarship application fee ለመክፈል ከ Alibaba, Amazon እና የመሳሰሉ የኦንላይን ገበያዎች ላይ ክፍያ ለመፈጸም እንዲሁም ለሌሎች ማንኛውንም በ online የሚከፈሉ ክፍያዎች ለመክፈል ፈልገው ተቸግረዋል

እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሄ አለ!

በVisa card, Mastercard ወይም በ Payoneer እንደራስዎ ሆነን ክፍያዎን እንፈጽምሎታለን!

- በ ቴሌግራም  አድራሻችን @StraightouttaNazreth
-በ ስልክ ቁጥራችን +251934729413 ይደውሉ

Niya online payment
34.9K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ