Get Mystery Box with random crypto!

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸው ተገ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸውን የገለፀው የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ነው፡፡

ከእነዚህ መካከል 10 የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች ከክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክክር ጉባኤ በኋላ ወደስራ የገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬን በጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ እንዲሁም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ 19 ሚሊየን 806 ሺህ 957 ከ80 ዶላር ማግኘት መቻሉም ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1