Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሶማሊያን ለቀጣይ 4 ዓመታት ለመምራት አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ዳግም ከተመረጡት ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ጋር በጋራ ቀጣናዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ በድጋሚ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እወዳለሁ። የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንደምንሠራ እምነቴ ነው።"ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1