Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.97K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 147

2022-05-18 20:23:12
ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር መሆናቸው ተሰምቷል

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከ2 ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ዛሬ ምሽት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤ የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል። ከአማራ ክልል የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም ፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገ ሙከራ አለመሳካቱን ቢቢሲ አስነብቧል።
ቢቢሲ

@Esat_tv1
@Esat_tv1
32.1K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 16:55:11
በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል

ጠ/ሚ ዐቢይ

በኢትዮጵያ የተጀመረው በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ በሀገራችን ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች አሉ ብለዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.7K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 14:14:29 አሸባሪው ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው የተለያዩ አካባቢዎች በተወሰደ እርምጃ ህዝቡ አንፃራዊ ሰላም እያገኘ ነው-ኮ/ል አበበ ገረሱ

የአሸባሪው ሸኔ ቡድን በሚንቀሳቀስባቸው ዞኖች በተወሰደ እርምጃ ህዝቡ ከነበረበት ስጋት እና ጭንቀት በመላቀቅ አንፃራዊ ሰላም እያገኘ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ገለጸ።

የቢሮ ምክትል ሃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ አሁን ላይ የጸጥታ ሃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር እየወሰደ ባለው የተቀናጀ እርምጃ ሸኔ እንደበፊቱ ስጋት አይሆንም ብለዋል።

በክልሉ ጉጂ ዞኖች፣ በአራቱ ወለጋ ዞኖች፣ በሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በከፊል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሸኔ ቡድንን ከአካባቢው የማጽዳት እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

ህዝቡ ከመንግስት እና ከፀጥታ ሃይሉ ጋር የቆመ እና የሸኔ ቡድን እያደረሰበት ከነበረው ግፍ እና በደል ለመላቀቅ በእርምጃው ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

ማህበረሰቡ በሸኔ ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ መረጃ በመስጠት እና ምግብን ከፀጥታ ሃይሉ ጋር ተቋድሶ በመብላት አብሮ ውሎ በማደር እርምጃው ውጤታማ እንዲሆን አድርጓል ነው ያለት።

በአከባቢዎቹ ተገድቦ የቆየው የህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅሳቃሴ ወደ መደበኛው ቦታ እየተመለሰ መሆኑን ኮሎኔል አበበ ገረሱ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ሸኔ የፀጥታ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል አበበ ገረሱ÷ ሆኖም ግን በተወሰኑ አካባቢዎች የቆየውን የጸጥታ ችግር ምክንያት በማድረግ ዝርፊያ ለመፈጸም የሚሞክሩ ግለሰቦች መኖራቸውን አንስተዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
47.7K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 14:14:28
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
43.0K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 14:14:22
በርሶ ፎቶ በፍቅረኛዎ ፎቶ ወይም በሚያደንቁት ሰው ምስል አሳምረን እንሰራለን! ከ ናተ ሚጠበቀው ፎቶውን መላክ ብቻ ነው

ስልክ 0949378569
0918698501

ማሰራት የምትፈልጉ ፎቶአቹን በዚህ Username ላኩልን
@Yaska_yasa
@Smith_Rio

የተሰሩ ሰዓቶችን ለመመልከት

https://t.me/joinchat/AAAAAFGMUgiL2c0_OopkxQ
43.8K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 22:51:54
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር የፈረመቻቸውን ስምምነቶች እና የፋይናንስ ድጋፍ ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮልን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2013 ዓ፣ም ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር የፈረመቻቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት፣ የወታደራዊ ፋይናንስ ስምምነት እና የፋይናንስ ድጋፍ ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮል ዛሬ ማጽደቁን የዋዜማ ሪፖርተር ዘግባለች።

የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነቱ በወታደራዊ ልምምዶች፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ በወታደራዊ መረጃ፣ ልውውጥ፣ በወታደራዊ ኮምንኬሽን ወዘተ የሁለትዮሽ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ነው።

የወታደራዊ ፋይናንስ ስምምነቱ ደሞ ኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቱርክ ሰራሽ የመከላከያ መሳሪያዎችን ከቱርክ ኩባንያዎች እንድትገዛና ያለ ቱርክ ፍቃድ መሳሪያዎቹን ለሦስተኛ ወገን አሳልፋ እንዳትሰጥ የሚከለክል ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
58.4K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 15:31:30
በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት መካከል የ19 ሚሊዮን ዩሮ የዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ

በኢትየዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ ሦስት የተለያዩ ፕሮጀክቶች የፈረንሳይ መንግስታት 19 ሚሊየን ዩሮ ወይንም 1 ነጥብ 02 ቢሊየን ብር ዕርዳታ ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የዕርዳታ ስምምነት አድርጓል።

የመጀመሪያው ፕሮጀክት የ 8 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች ለመጠገንና ለመንከባከብ የሚያስችል ሲሆን ቅርሶቹ ለቱሪስቶችና ለጎብኝዎች በሚያመች መልኩ ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው፡፡

ሁለተኛው ፕሮጀክት የ10 ሚለየን ዩሮ ድጋፍ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሀይልን የሰራተኛውን ክህሎት በማሳደግ የተቋሙን ውጤታማነትን ለማጠናከርና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚያግዝ ነው፡፡

ይህን ለማድረግ እንዲቻል የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያስገነባውን የስልጠና ተቋም ግንባታና የውስጥ መገልገያ መሳሪያዎች ለማሟላትም የሚውል የፕሮጀክት ድጋፍ ነው፡፡

ሶስተኛው ፕሮጀክት የአንድ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ሲሆን በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራትን ኤጀንሲን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የሲቪል ማህበራትን አቅም በመገንባትና በማጠናከር ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያግዛቸው ነው፡፡

ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰውና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ መንግስት ልማት ድርጅት ሀላፊ ቫሌሪ ቲአዎ የፈረንሳይ አምባሳደር በኢትዮጵያ ሬሚ ማስቹዌክስ በተገኙበት መፈረማቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
65.2K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:27:30 ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ገለፁ።

bbc Amharic

ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ገልፀዋል። ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ጄኔራል ተፈራ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በቅርቡ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው መስራታቸው ይታወሳል ።እንደ ወ/ሮ መነን ገለፃ ከሆነ ጄኔራል ተፈራ ያገኟቸው ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረዋቸዋል። ከዚያ በኋላ ግን የደረሱበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ተናግረዋል ።

ጄኔራል ተፈራ ሞሞ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥነት ከተነሱ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።ወ/ሮ መነን የባለቤታቸውን መጥፋት አስመልክቶ ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ቢጠይቁም ግለሰቡ "በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ" እንደገለፁላቸው ይናገራሉ።በአሁኑ ሰዓትም ባለቤታቸውን ለማግኘት ሊኖሩበት ይችላሉ ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው።ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ባለቤታቸው ተናግረዋል።ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል።"እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን ጤናው ሁኔታ ነው" ብለዋል።

የጄነራሉን መሰወር በተመለከተ የፌደራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስካሁን ያሉት ነገር የለም።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ለዓመታት በከፍተኛ መኮንንነት ያገለገሉት ብርጋዲዬር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአስር ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ጋር ተከሰው ለዓመታት በአስር ላይ ቆይተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎም ከእስር ተለቀው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።በቅርቡም የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመግባት ጥቃት በሰነዘሩበት ጊዜ የክልሉን ልዩ ኃይል በበላይነት ሲመሩ የነበሩ ሲሆን፣ ከጥቂት ወራት በፊት ደግሞ ከዚሁ ኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸው ይታወሳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
64.9K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:08:15 #AmharaRegion #እንድታውቁት

tikvah

ከዛሬ ግንቦት 9 ጀምሮ በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ይካሄዳል።

ይኸው የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በክልሉ ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው ባሉ የምዝገባ ማዕከላት መሳሪያውን ማስመዝገብ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምዝገባው የአማራን ህዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ አመልክቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
62.0K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 19:26:13
የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ጆ ባይደን ወሰኑ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት ዶናልድ ትራምፕ የተወሰነዉን ውሳኔ በመቀልበስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቅደዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ሊመለሱ ይችላሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በአልሸባብ የታጣቂ ቡድን መሪዎች ላይ ዒላማ ለማድረግ ከፔንታጎን የቀረበላቸዉን ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸዉን በፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆነችዉ አድሪያን ዋትሰን እንደተናገሩት "እንደገና ለማስጀመር የወሰነው የኃይላችንን ደህንነት እና ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ብሎም ለአጋሮቻችን ቀልጣፋ ድጋፍ ለመስጠት ነው" ብለዋል።

አክለዉም "በአልሸባብ ላይ የበለጠ ውጤታማ ትግል" ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት እሁድ እለት አዲሱን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን መምረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
71.4K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ