Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.97K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-26 14:49:46
በጾም ወቅት ምን ልጠቀም ብለዉ እያሰቡ ከሆነ በአንድ ማንኪያ ከ23 ግራም በላይ ፕሮቲን ሊያገኙበት የሚችሉትን 100% የቪጋን ፕሮቲን አመጣንልዎ።

በከፍተኛ ጥራት የተመረተ

አሁኑኑ ለማዘዝ 9369 ላይ ይደውሉልን፣ የዘርፉ ባለሟያዎች ትክክለኛዎቹን ምርቶች ለመምረጥ እና ፈጣን አቅርቦትን ለማዘጋጀት ይረዳዎታል።

የሚያስፈልገው ጓደኛ ካለዎት share ማድረግዎን አይዘንጉ!


አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ 9369


+251966113766

Join  https://t.me/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5
31.5K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 14:49:13
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://t.me/Poppycarmarket

0911248768   ይደውሉልን
29.4K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 18:28:14
አቶ ታዬ ደንደአ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት' ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በጸጥታ ሀይሎች ታህሳስ 2 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ “የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት” ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

በክሱ ላይ ፤ “ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር” የሚል ተካቷል፡፡

አቶ ታዬ ደንደኣ በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል።

ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።ፍርድ ቤቱም በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጾ፤ ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
43.0K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 11:16:56
ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት

አቶ ጌታቸው ረዳ

በማህበራዊ ሚዲያ " ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ድርድር እየተካሄደ ነው " የሚሉት መረጃዎች ፍጹም ሐሰተኛ ናቸው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ተናግረዋል።

ብልፅግና እና ህወሓት ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው "  እነዚህ ንግግሮች ከውህደት ጋር የተያያዙ አይደሉም " ብለዋል።

" የቅርብ ጊዜው ንግግራችን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ስለማድረግ ነው። ውህደት አጀንዳም ሆኖ አያውቅም " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ስላላቸው የስራ ግኝኑት በተመለከተ ፥ " ጥሩ የሥራ ግንኙነት ነው ያለን። የራሳችን የሆነ ልዩነት አለን። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉን " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ስምምነት አብረን እንድንሠራ ዕድል ስለሰጠን፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችን ምንም ይሁኑ ምን አብረን እንድንሠራ አስችሎናል። ይህም ወደፊት ይቀጥላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ጌታቸው በጦርነቱ ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ በሙሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል።

" ማንም ሰው ቢሆን፤ እኔን ጨምሮ መጠየቅ አለብን። ማንም ነጻ እንዲሆን መፈቀድ የለበትም። ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " ሲሉ ገልጸዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
44.8K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 11:16:55
[CREATINE MONOHYADRATE ]

ጡንቻን ለመገንባት እና ጉልበት ለማግኘት፤ ለሰውነትዎ የሚያስፈልገውን ይስጡት!

ጥንካሬ፣ብርታት እና ፈጣን የሰዉነት ጥገና ያስፈልገኛል ብለዉ ካሰቡ ክሬቲን ይገባዎታል
የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንደሚያሳየዉ ክሬቲን የሚጠቀሙ አትሌቶች እና ስፓርተኞች 23 % የተሻለ አፈጻጸም እና ጥገና ያሳያሉ!

ለነፃ የምክር አገልግሎት እና የተሟላ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን።

አድራሻችን;- ሆሳዕና ጮራሞ ሕንፃ 1 ፎቅ የቤት ቁጥር 07 ጎራ በማለት የሚፈልጉትን ያገኛሉ።

+251966114766

9369 ላይ ይደውሉ  
41.1K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 20:14:35
ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
27.2K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 10:21:34
ሐሰተኛ መረጃ

በአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው።

ሰሞኑን በአማራ ክልል ‘የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታትን ይመለከታል’ በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ደብዳቤ የተጻፈ በማስመሰል የወጣው መረጃ ፍጹም ሐሰት መሆኑን ክልሉ አረጋግጧል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህም በክልሉ ያሉ የጸጥታ ኃይሎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተው እያመጡት ያለው ውጤት ኪሳራ ያደረሰባቸው ኃይሎች በሚልሻውና ህብረተሰቡ ውስጥ መደናገርን ለመፍጠር አልመው የፈጸሙት እኩይ ድርጊት መሆኑ ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
39.4K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 18:33:49
ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
44.4K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 13:54:25
የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል።

ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
44.8K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:27:43
በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የለኝም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

አጭበርባሪዎች የባንኩን ስምና አርማ እንዲሁም ቀለማት በመጠቀም ሀሰተኛ ገጾችን በመክፈት የማጭበርበር ወንጀል እየፈፀሙ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ለህበረተሰቡ በማሳወቅ ላይ እንደሚገኝም ባንኩ ገልጿል።

በምስሉ የተመለከተው በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ሀሰተኛ መሆኑን የገለፀው ባንኩ፤ ይህ ሀሰተኛ ገፅ አባላትን ስታስገቡ (Add member) ሽልማት ታገኛላችሁ በሚል የማጭበርበሪያ መልእክት የተከታዮቹን ቁጥር በማሳደግ ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ባንኩ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው ግልፆ፤ ደንበኞች የባንኩን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እና ከአጭበርባሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
30.3K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ