Get Mystery Box with random crypto!

በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የለኝም የኢትዮጵያ ንግድ ባን | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ የለኝም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው አስታውቋል፡፡

አጭበርባሪዎች የባንኩን ስምና አርማ እንዲሁም ቀለማት በመጠቀም ሀሰተኛ ገጾችን በመክፈት የማጭበርበር ወንጀል እየፈፀሙ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ለህበረተሰቡ በማሳወቅ ላይ እንደሚገኝም ባንኩ ገልጿል።

በምስሉ የተመለከተው በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ሀሰተኛ መሆኑን የገለፀው ባንኩ፤ ይህ ሀሰተኛ ገፅ አባላትን ስታስገቡ (Add member) ሽልማት ታገኛላችሁ በሚል የማጭበርበሪያ መልእክት የተከታዮቹን ቁጥር በማሳደግ ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ባንኩ በሲቢኢ ብር ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንደሌለው ግልፆ፤ ደንበኞች የባንኩን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እና ከአጭበርባሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1