Get Mystery Box with random crypto!

ኢራን እስራኤል ላይ የድሮን ጥቃት ከፈተች ከሰምኑ ውጥረት ውስጥ በከረሙት  ኢራንና እስራኤል መ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ኢራን እስራኤል ላይ የድሮን ጥቃት ከፈተች

ከሰምኑ ውጥረት ውስጥ በከረሙት  ኢራንና እስራኤል መካከል ጦርነቱ ስድስት ሰአት ተኩል ላይ በይፋ ጀምሯል።

ኢራን ወደ እስራኤል በሺወች የሚቆጠሩ  ሮኬት እና ሚሳኤሎችን ተኩሳለች።

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ወደሚገኙት  የጎላን ተራሮች በደርዘን የሚቆጠሩ  ሮኬቶችን እየስወነጨፈ ነው።

አሜሪካ ተጨማሪ ሃይሏን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አስጠግታለች።

ኢራቅና ዮርዳኖስ   የአየር ክልላቸውን  በጊዜያዊነት ዘግተዋል።

የእስራኤል የአየር ክልልም ከደቂቃዎች በኋላ ሙሉ ለሙሉ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ድሮኖች ወይም ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ እስራኤል ለመድረስ 1 ሺህ 800 ኪ.ሜ. ርቀት ያህል መጓዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ፥ ይህም ሰዓታት ሊወስድ እንደሚችልም ነው የተገለፀው።

አልጀዚራ እያንዳንዱን ክስተት በቀጥታ ስርጭት እያስመለከተ ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1