Get Mystery Box with random crypto!

38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፏል በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፏል

በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን እንዳጡ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

ትላንት ሰኞ በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ " ጎዶሪያ " በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ኤምባሲው ፥ በየዓመቱ ከ200 ሺ የሚበልጡ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ባህር ዳርቻ የኤደን ባህረ ሰላጤ በመነሳት መካከለኛው ምስራቅ አገራት ለመድረስ በየብስ እና በባህር አደገኛ ጉዞ ያደርጋሉ ብሏል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በጀልባ መስመጥ አደጋ ብቻ የ189 ዜጎቻችን ሕይወት እንዳለፈ ጠቁሟል።

በየጊዜው የሚደርሰው አደጋ እንዳለ ቢሆንም የፍልሰተኞቹ ቁጥር ግን አሁንም እየጨመረ እንደሆነ ገልጿል።

ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

የፍትህ አካላት ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ከገጠራማ የአገራችን አካባቢዎች ዜጎቻችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1