Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.97K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-12 18:36:12
ኢትዮጵያን ጨምሮ በ5 የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተገለፀ

በፈረንጆቹ 2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ በ5 የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስታውቋል።

ከፍተኛ የምግብ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከተከሰተባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ዝምባብዌ፣ ሴራሊዮን ማላዊ፣ ናይጄሪያ እና የምግብ ሸቀጦች ግሽበቱ 29.4 ደርሷል የተባለባት ኢትዮጵያ ከ1 እስከ 5 ባለው ደረጃ ሲቀመጡ ጋና፣ አንጎላ፣ ብሩንዲ፣ ጋምቢያ እና ጊኒ ከ6 እስከ 10ኛ ደረጃዎች ላይ መቀመጣቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
41.4K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 17:32:03 ​​በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም

አዲስ አበባ ፓሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ በፋኖና በፓሊስ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አንድ ሲቪልና ሁለት ታጣቂዎች ሲገደሉ፣ በሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የ“ፋኖ” አመራርና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሚሊኒየም አዳራሽ አጠገብ ከፀጥታ አካላት ተኩስ እንደከፈቱ፣ በ “ፋኖ” በኩል ሁለት ታጣቂዎች ሲገደሉ አንድ በቁጥጥር ስር እንደዋለ፣ በመንግሥት በኩል ሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ በንጹሐን በኩል ደግሞ አንድ አሽከርካራ እንደተገደለ፣ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት ቃል፣ “ የተገደሉት የ “ፋኖ” ቡድን አመራርና አባላት ናቸው። አመራሩ ናሁሰናይ አንዳርጌ ነው። ሌላው አቤኔዘር ጋሻው የተባለው ነው፣ እዛው ቦታው ላይ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሂወቱ አልፏል። ሀብታሙ አንዳርጌ ግን ምንም አልሆነም በቁጥጥር ስር ውሏል ” ብለዋል።

የ “ፋኖ” አመራርና አባላት የነበራቸውን እንቅስቃሴ ሲያስረዱም ኮማንደሩ፣ “ በከተማው ውስጥ ነው የሚንቀሳቀሱት የነበረው። በከተማው ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ጥፋቶች ለማጥፋት ነው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበረው ” ነው ያሉት።

አክለውም፣ “ እነርሱን ለመያዝ በተደረገው ሂደት ቦሌ ወረዳ 3 ሳጅን አራርሳ ተሾመና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ የሚባሉ ሁለት የፓሊስ አባላት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ከእነርሱ (“ፋኖ”) በተተኮሰ ጥይት ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ እሱም ብቻ አይደለም አንድ አሽከርካሪ እንዲጭናቸው ሲያስገድዱት ‘አልተባበርም’ ስላለ መኪና ውስጥ በጥይት መትተውት ሞቷል። የአንድ ግለሰብ ተሽከርካሪ መስታውት በጥይት መትተውታል። ሙሉ ለሙሉ ጉዳት ደርሶበታል። ሰውየው ግን ምንም የሆነው ነገር የለም ” ነው ያሉት።

“ ማኀበረሰቡ ከፓሊስና ከፀጥታ አካላት የሚተላለፉ መረጃዎችን በቁም ነገር ማዳመጥ፣ አካባቢውን ማዬት መቻል አለበት። በሰላምና በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም። እነዚህ ሰዎች መካከላችን አሉ። ይሄ አንዱ ማሳያ ነው። ቦሌ መሀል ከተማው ላይ እንግዲህ እየኖሩ ነው የነበረው ” ብለዋል ኮማንደር ማርቆስ።

“ እነዚህ ሰዎች መንፈስ አይደሉም። በተሽከርካሪያቸው ሲወጡ ሲገቡ ይታያሉ። ግን ፓሊስ በራሱ ነው ሲከታተተል የነበረው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፤ አሁንም ማህበረሰቡ አካባቢውን መጠበቅ አለበት ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
39.8K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 13:45:33
በጽንፈኛው ኃይል አመራር እና አባል ላይ እርምጃ ተወስዷል

ፖሊስ

በፅንፈኛው ኃይል አመራርና አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በተወሰደው እምርጃም÷ የፅንፈኛው አመራርና አንድ የቡድኑ አባል መገደላቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሏል ነው ያለው ፖሊስ፡፡

በዚህም ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት የፅንፈኛው ቡድን አባላት በአዲስ አበባ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው እየተንቃሰቀሱ መሆኑን የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል እንደተደረሰበትም ፖሊስ ጠቅሷል፡፡

የሽብር ተግባራቸውን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ፅንፈኞቹ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል መሞቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም አቤኔዘር ጋሻው አባተ የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

ፅንፈኞቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ሲቆስሉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ፅንፈኞቹ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በፅንፈኛው አባላት ተገድለዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.1K viewsedited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 11:38:50 ​​አቶ በቴ ኡርጌሳ በበርካታ ጥይት ተደብድበዉ ህይወታቸዉን እንዳጡ የህክምና ባለሙያ ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ውስጥ በምትገኘው የትውልድ ከተማቸው መቂ ረቡዕ ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም. ተገድለው የተገኙት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በበርካታ ጥይት መመታታቸውን የሕክምና ባለሙያ እና የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ገለጹ።

አስከሬናቸው ከመቂ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቆሻሻ መጣያ አካባቢ የተገኘው አቶ በቴ ኡርጌሳ፣ ጭንቅላት ላይ አምስት በጥይት ምት የተፈጠሩ ጉዳቶችን መመልከታቸውን ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያ ተናግረዋል።

“ጭንቅላቱ ላይ አምስት ቁስለት፣ ወገቡ ላይ ሦስት ቦታ፣ በግራ ጎኑ አንድ ትልቅ ጉዳት፣ ከወገቡ ወደታች እና ታፋው ላይም ተጨማሪ አንዳንድ ጉዳት በአጠቃላይ 11 የሚሆኑ ቁስለቶች ታይተዋል።”

የሕክምና ባለሙያው ሁሉም ጉዳቶች በጥይት የተፈጠሩ መሆን አለመሆናቸውን የተጠየቁ ሲሆን፣ “ለእኛ እንደዚያ ይመስላሉ። ገሚሶቹ ጥይቱ በገባበት የተፈጠሩ፣ ገሚሶቹ ደግሞ ጥይቱ የወጣበት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ጥይት የገባበት ነው ማለት አይደለም” ብለዋል።

እኚሁ ባለሙያ አቶ በቴ ጭንቅላታቸው ላይ አምስት ጉዳቶች ቢኖሩም፣ ፊታቸው ላይ ግን ምንም ዓይነት ጉዳት አለመመልከታቸውን ተናግረዋል።

በአቶ በቴ አስከሬን ላይ የፎረንሲክ ምርመራ እንዳልተካሄደ ገልጸውም “በሰውነታቸው ላይ የቀረ ጥይት መኖር አለመኖሩን መለየት ይከብዳል” ሲሉ ለቢቢሲ መናገራቸውን ከዘገባው ተመልክቷል። የህክምና ባለሙያው ጨምረውም “ጭንቅላታቸው ላይ የታየው አምስት ጉዳት ግን ሰውነታቸው ውስጥ የቀረ ጥይት መኖሩን ጥርጣሬ ይፈጥራል” ብለዋል።

የፖለቲከኛውን ግድያ ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል በፖለቲከኛው ግድያ ላይ የመንግሥት ኃይሎች አሉበት መባሉን ውድቅ አድርጓል።

የአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ አካል ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዲፈቅዱ አሜሪካ ጠይቃለች። የኦሮምያ ክልል መንግሥት በመቂ ከተማ አስከሬናቸው ተጥሎ የተገኙት ፖለቲከኛ የተገደሉት “ባልታወቁ ጥቃት አድራሾች” እንደሆነ ገልጿል።

የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሌላ ግለሰብ በበኩላቸው ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ረቡዕ ጠዋት ከነዋሪዎች ባገኙት መረጃ መሠረት፣ ሁለት ሰዓት አካባቢ አስከሬኑን ማግኘታቸውን ተናግረዋል። እኚሁ የቤተሰብ አባል አስከሬኑን ሲያገኙት አካሉ ብዙ ቦታዎች ላይ ቆስሎ መመልከታቸውንም ገልጸዋል።

“አካሉ ላይ የተገኙትን ጉዳቶች ትክክለኛ ቁጥር የአስከሬን ምርመራ ውጤት ነው የሚያሳየው። ቢያንስ በስድስት ጥይቶች መመታቱን ግን ፎቶዎች ተነስተው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተለቀቁት ማየት ችለናል።

የመቂ ከተማ ከንቲባ አቶ ዲልቦ ኡርጌሳ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃለ ምልልስ ግድያው የተፈጸመው ቤተሰብ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ገልጸው፣ ጉዳዩን ለማጣራት ምርመራ እንደሚያደረግ ተናግረው ነበር።

የአቶ በቴ የቤተሰብ አባል ግን ምንም ዓይነት የቤተሰብ አለመግባባት እንደሌለ ተናግረው “ሐቁ እንዳይወጣ መንገድ ለማሳት፣ ሕዝብ መሃልም መደናገር ለመፍጠር ያለመ ነው” ሲሉ አስተባብለዋል። “እርሱን ገድለው ያልጠገቡ፣ እውነቱን ለማጥፋት የፈለጉ” ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ቢቢሲ አማርኛ

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.1K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:21:25
ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት” ናት አሉ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ስጋት” መሆኗን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ድርድር እንደማይኖር እና ሶማሊያ ሉዓላዊነቷን ለድርድር እንደማታቀርብም ተናግረዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ ሞሐመድ ይህንን ያሉት የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም. ለአገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ነው። 24 ደቂቃ ገደማ የቆየው የፕሬዝዳንቱ ንግግር የአገር ውስጥ እና ቀጣናዊ ጉዳዮችን የዳሰሰ ነበር።

የባሕር በር ለማገኘት ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው እና አምባሳደሯን እንድታስወጣ የተደረገችው የኢትዮጵያ ጉዳይም በፕሬዝዳንቱ ንግግር ውስጥ ተነስቷል።

“የኢትዮጵያ መሪዎች ወደ ቀልባቸው መመለስ አለባቸው” ያሉትን ሐሴን ሼህ፤ ግጭት እየፈጠረች ያለችው ኢትዮጵያ እንጂ ሶማሊያ እንዳልሆነች ለዓለም እየተናገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
29.9K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:21:03
በጾም ወቅት ምን ልጠቀም ብለዉ እያሰቡ ከሆነ በአንድ ማንኪያ ከ23 ግራም በላይ ፕሮቲን ሊያገኙበት የሚችሉትን 100% የቪጋን ፕሮቲን አመጣንልዎ።

በከፍተኛ ጥራት የተመረተ

አሁኑኑ ለማዘዝ 9369 ላይ ይደውሉልን፣ የዘርፉ ባለሟያዎች ትክክለኛዎቹን ምርቶች ለመምረጥ እና ፈጣን አቅርቦትን ለማዘጋጀት ይረዳዎታል።

የሚያስፈልገው ጓደኛ ካለዎት share ማድረግዎን አይዘንጉ!


አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ 9369


+251966113766

Join  https://t.me/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5
26.7K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 17:09:33
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ

ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

" በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረገው ግድያ ቀጥሏል " ያለው ኦነግ የታወቂውና ተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሳይረሳ እና ቤተሰቦቹ እስካሁን ፍትህ ሳያገኙ የበቴን ኡርጌሳን ግድያ መስማት እጅግ አሳዛኝ ነው ብሏል።

ጃል በቴ በተወለዱበት መቂ ከተማ #በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

" ምንም እንኳን ሁኔታው ​​​​ለሁላችን እጅግ በጣም ከባድ ቢሆንም በግድያው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረግን ነው " ሲል ገልጿል።

" ሁሉም የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እና ሰላም ወዳድ ህዝቦች አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ " ጥሪ አቅርቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
41.5K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 12:10:51
የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።

" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው በከተማ ተገድለው ተጥለው ነው የተገኙት " ተብሏል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር በዋስ ከእስር ተለቀው ነበር። ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይተ ተመተው ተገድለዋል። ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
43.8K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 21:27:21
ነገ የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል

@Esat_tv1
@Esat_tv1
46.4K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 20:26:56
ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ተወዳጁ ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ድምጻዊ ሙሉቀን በሚኖርበት አሜሪካ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
46.7K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ