Get Mystery Box with random crypto!

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ ( | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።

" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው በከተማ ተገድለው ተጥለው ነው የተገኙት " ተብሏል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር በዋስ ከእስር ተለቀው ነበር። ትላንት ምሽት በመቂ ከተማ በጥይተ ተመተው ተገድለዋል። ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

@Esat_tv1
@Esat_tv1