Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.97K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-04-08 18:18:53 ኢድ ሙባረክ

የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ የኢድ አልፊጥር በዓል የፊታችን እሮብ ሚያዝያ 2 መሆኑ ተገልፆል::

ነገ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 የረመዳን የመጨረሻው 30ኛ ቀን ሆኗል

አላህ ፆማችንን ይቀበለ

Ustaz Abubeker Ahmed

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.5K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 17:00:00
የዒድ አልፊጥር ሰላት ከጠዋቱ 2:30 ይሰገዳል። እንደየ አካባቢያችሁ ርቀት ይህንን ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ እንድታደርጉ ምክር ቤታችን ያሳስባል

በዓሉም ጨረቃ ዛሬ ከታየች ነገ ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.8K viewsedited  14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 12:09:58
1 ሺህ 445ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል ማክሰኞ ወይም ረቡዕ እንደሚከበር ተገለጸ

1 ሺህ 445ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል ማክሰኞ ወይም ረቡዕ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የፊታችን ሰኞ ጨረቃ ከታየች በዓሉ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን የሚከበር ሲሆን፥ ጨረቃ ሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ሚያዝያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚከበር አስታውቋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከበዓሉ ጋር አያይዞ እንደገለፀው በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው የሰላም ችግር በውይይት እንዲፈታ ጠይቋል።

በተፈጠረው ግጭት እየሞቱም ሆነ እየተፈናቀሉ የሚገኙት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው በግጭት እየተሳተፋ የሚገኙ አካላት፥ ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲቀርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለው በዓሉን ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊከበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
29.2K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 12:05:38
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከሚደረግ የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ተዘግተው የነበሩ መገዶች ተከፍተዋል

ሰልፉ መጠናቀቁን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
28.3K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 11:12:30
በመዲናዋ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የጋራ ግብረ ሃይሉ አስታወቀ

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በስኬት እና በሰላም እንዲጠናቅ ለማስቻል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡

የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የታደሙበት የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን ግብር ኃይሉ አስታውቋል፡፡

በተያዘው ዓመት በርካታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት የታደመባቸው ልዩ ልዩ የአደባባይ ሁነቶች ሃይማኖታዊ በዓላት እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከናወናቸው የሚታወስ ነው፡፡

ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደውን ትብብር በማድረጉና በተለይ መላው የፀጥታ አካላት ድካማቸውን ተቋቁመው ሃላፊነታቸው በትጋት በመወጣታቸው በ2016 ዓ.ም መዲናዋ ያስተናገደቻቸው አበይት ኩነቶቹ ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ማድረግ እንደተቻለ ተጠቁሟል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው እና በርካታ ህዝብ የታደመበት ሰልፍም በሰላም እንደጠተናቀቀ ግብረ ኃይሉ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሰልፉ በሠላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር እንዲሁም ሃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት አመራርና አባላት የጋራ ግብረ ሃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
27.5K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 11:12:26
መኪናዎን #በአስቸኳይ መሸጥ ከፈለጉ ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ሞልተው  

0911407105  ላይ ደውለዉ ያሳውቁን። ስለመረጡን እናመሰግናለን

የመኪናው ዓይነት___
የመኪናው ሞዴል___
ትራንስሚሽን___
የዞረ/ያልዞረ___
የተነዳው ኪ.ሜ___
ስለመኪናው አቋም አጭር ማብራሪያ___
በተለያየ አቅጣጫ የተነሳ ፎቶ___
የመሸጫ ዋጋ___
የባለቤት ስልክ___


0911407105   ይደውሉልን

➧ቻናላችንን በመቀላቀል የተለያዩ አዳድስና ያገለገሉ መኪኖችን ማግኘት ይችላሉ !!!  


https://t.me/Poppycarmarket
24.3K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 11:12:17 ከቅርብ አመታት ወዲህ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለትምህርት አሰጣጥ ዘዴ መፍትሄዎችን ማምጣት ችሏል። ተቋማችንም ከዘመኑ ጋር አብሮ በመጓዝ የተለያዩ ቋንቋዎችን  በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እድገት ተማሪና አስተማሪን በቀላል መንገድ በማስተሳሰር መማርን ቀላልና ተደራሽ አድርጎ መቷል።እርሰዎም ፈጥነው በመመዝገብ ፍላጎትዎን ያሳኩ!
   እንግሊዘኛ
   አረብኛ
   አፋን ኦሮሞ
   አማርኛ  ቋንቋን ባሉበት ሆነው ይማሩ!!

ለበለጠ መረጃ፦ 0933666662ወይም
                        0932878889 ይደውሉ

በአካል መምጣት ከፈለጉ
አ.አ፡ቤተል፡ AJ ሞል አራተኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል

  ብራይት የስልጠና ማዕከል
  ለብርሀናማ ህይወት ትክክለኛ ቦታ!!

https://t.me/brighttraining90
25.3K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 17:26:51
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከመጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሥራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን አስታውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
35.6K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 16:56:28 ነገ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻዎች እንደሚኖሩ ተገንዝበው ለፀጥታ አካላት የፍተሻ ሥራ ተባባሪ እንዲሆኑ ግብረ ሐይሉ አሳስቧል፡፡

በተመሳሳይ በሰልፉ ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ አሽከርካሪዎች መረጃው ኖሯቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትእዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

በመሆኑም በዕለቱ ከንጋቱ 11፡00 ሰአት ጀምሮ የድጋፍ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ:-
– ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሔራዊ ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ፣
– ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ፣
– ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣
– ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፣
– ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ፣
– ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት፣
– ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት፣
– ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት ላይ፣
– ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ፣
– ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣
– ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
– ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሟቸው አቅጣጫ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ዋዜማው ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰልፉ ፍፃሜ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ወይም ማሳደር የተከለከለ ነው፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ ጥሪ ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
36.1K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 16:05:07
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከሲስተም ማዘመኛ ጋር በተያያዘ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከ64 ሺህ እስከ 71 ሺህ ብር ወስደው ያልመለሱ ሰዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

የግለሰቦቹን ምስል እና ሌሎች መረጃዎችን ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ፡- https://combanketh.et/customer-round-five

@Esat_tv1
@Esat_tv1
34.4K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ