Get Mystery Box with random crypto!

1 ሺህ 445ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል ማክሰኞ ወይም ረቡዕ እንደሚከበር ተገለጸ 1 ሺህ 445 | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

1 ሺህ 445ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል ማክሰኞ ወይም ረቡዕ እንደሚከበር ተገለጸ

1 ሺህ 445ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል ማክሰኞ ወይም ረቡዕ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የፊታችን ሰኞ ጨረቃ ከታየች በዓሉ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን የሚከበር ሲሆን፥ ጨረቃ ሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ሚያዝያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚከበር አስታውቋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከበዓሉ ጋር አያይዞ እንደገለፀው በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው የሰላም ችግር በውይይት እንዲፈታ ጠይቋል።

በተፈጠረው ግጭት እየሞቱም ሆነ እየተፈናቀሉ የሚገኙት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው በግጭት እየተሳተፋ የሚገኙ አካላት፥ ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲቀርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለው በዓሉን ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊከበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1