Get Mystery Box with random crypto!

ሐሰተኛ መረጃ በአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ሐሰተኛ መረጃ

በአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው።

ሰሞኑን በአማራ ክልል ‘የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታትን ይመለከታል’ በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ደብዳቤ የተጻፈ በማስመሰል የወጣው መረጃ ፍጹም ሐሰት መሆኑን ክልሉ አረጋግጧል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህም በክልሉ ያሉ የጸጥታ ኃይሎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተው እያመጡት ያለው ውጤት ኪሳራ ያደረሰባቸው ኃይሎች በሚልሻውና ህብረተሰቡ ውስጥ መደናገርን ለመፍጠር አልመው የፈጸሙት እኩይ ድርጊት መሆኑ ተገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1