2022-05-26 21:07:33
አቶ ጃዋር መሀመድ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር) ከእስር ከተፈቱ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ " ለኡቡንቱ ቲቪ " የማህበራዊ መገናኛ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ
በዚሁ ቃለ ምምልስ ወቅት አቶ ጃዋር ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ እሳቸውን በተመለከተ ሲናፈሱ የነበሩ አሉባልታዎችን እንዲያጠሩ ነው " አቶ ጃዋር ከገዢው ፓርቲ ጋር መስራት ጀምሯል፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝቷል የተፈታውም ለዚህ ነው ፤ አሁንም እየሰራ ያለው የመንግስትን ስራ ነው " ስለሚባሉት ጉዳዮች ግልፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ጃዋር መሀመድ ፦
" እኔም ሰማቸዋለሁ አሉባልታዎቹን ። እኔ ከማንም ጋር የግል ቁርሾ የለኝም። የታሰርኩትም ቢሆን በፖለቲካ ልዩነት እንጂ በግል ፀብ አይደለም።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አልተገናኘንም፤ ሊያገኘኝ ከፈለገ ግን ሁሌም ዝግጁ ነኝ። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ብቻ ሳይሆን / ከዐቢይ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመሮም ጋር፣ ከደብረፅዮንም ጋር ከሁሉም በአሁን ወቅት በሀገራችን ባለው ግጭት ውስጥ እየተሳተፉ ካሉ ኃይሎች ጋር ተገናኝቶ ሀገራችንን ከጦርነት አስወጥቶ ወደ ሰላም እና ልማት ለመመለስ እድሉ ከተገኘ ከማናቸውም ጋር ለመስራት፣ ከማናቸውም ጋር ለመተባበር ፣ ከማናቸውም ጋር ለመነጋገር በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ።
እኔ ማልፈቅደው ግን ከማናቸውም ጋር አብሬ ጦርነት ማፋፋም አልፈልግም፤ ከማናቸውም ጋር።
ሁሉም በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ይሁኑ በጦርነት ውስጥ እያልተሳተፉ ያሉ ምሁራን እና ሊህቃን ወደ ሰላም ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፤ ከአንዳቸውም ጋር ግላዊ ጠብ የለኝም።
ስለዚህ ገዥው ፓርቲ ሀገር እየገዛ ነው ያለው ፤ ሀገር እያስተዳደረ ነው ያለው ፣ ሀገሪቷ ለገባችበት ችግር ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ገዢው ፓርቲ ነው፤ እንደመሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ፤ ወደመፍትሄ የምንገባ ከሆነ የእነሱ ተሳትፎ፣ የእነሱ ፍቃደኝነት ወሳኝ ነው።
ስለዚህ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አመራርም እንደ እዚህች ሀገር ዜጋም በሰላም ጉዳይ ላይ የሀገራችንን እጣፈንታ ወደፊት ማስተካከል ላይ ከገዢው ፓርቲም ጋር ሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሆነ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ከሚመሩ ቅድም እንዳልኩት ከደብረፅዮን ሆነ ፣ ከፃድቃን ሆነው፣ ከመሮም ሆነ፣ ከገመቹ ሆነ፣ ከተፈራ ማሞ ሆነ ፣ ከይልቃል ከፋለ ጋርም ሆነ ከማንኛውም ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፤ የሀገራችን አመራርም ለዚህ መዘጋጀት መቻል አለበት።
ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ለምን ከእከሌ ጋር ተነጋገርክ፣ እከሌ ሳይጣን ነው እከሌ መልአክ ነው በማለት እንደማያዋጣ ላለፉት 4 ፣ ላለፉት 2 ዓመታት ግልፅ ሆኗል።
ስለዚህ አሁንም ደግሜ የምለው ከማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ጋር ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ አመራር ጋር ህዝባችንን አሁን ከገባበት መቀመቅ እና ሰቆቃ ለማውጣት መስራት ያስፈልጋል።
እዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው ከማኛውም ኃይል ጋር እንሰራለን እንደ ድርጅትም እንደ ግለሰብም እንደ አመራርም፤ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ወደ ሰላም መንገድ ወደ ልማት እንዲመለሱ ባለኝ እውቀት እና ባለኝ ተሰሚነት መጥቀም እፈልጋለሁ።
ነገር ግን ለማንም ድርጅት ሆነ ግለሰብ መጠቀሚያ መሆን አልፈልግም ፤ ለማንም የጦር ማገዶ መሆን አልፈልግም ፣ የማንንም አንባገነናዊ አካሄድን፤ የማንም ጦረኛ አካሄድን መደገፍ አልፈልግም።
ወደ ሰላም መምጣት ከሚፈልግ አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፣ ይሄ ደግሞ ኩነኔ አይደለም ይሄ ትክክለኛ ነው ብዬ የማምነው ፤ ስለዚህ ጦርነቱ መቆም አለበት ጦርነት ቆሞ ወደ ድርድር መምጣት አለብን ቴክኒካል ነገሮች መነሳት አለባቸው ስለዚህ ለመነጋገር ጋሬጣ ሆነው ያሉ ነገሮች ተሰባብረው ድልድይ ተመስርቶ ሁላችንም ወደመነጋገር መግባት አስፈላጊ ነው። "
@Esat_tv1
@Esat_tv1
28.1K viewsedited 18:07