Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.49K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 153

2022-05-14 11:44:41
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
22.9K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 19:07:06 በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

ሚኒስቴሩ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ያደረገው ከሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ነባር ታሪፍ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ በአስፋልት መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 493 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር ብር 0 ነጥብ 532 ሆኗል ተብሏል፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር ታሪፍ 0 ነጥብ 548 የነበረው ወደ 0 ነጥብ 596 ከፍ ብሏል፡፡ በዚህም በኪሎ ሜትር የ 0 ነጥብ 049 ጭማሪ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል በደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 457 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 496 ሆኗል፡፡

በደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 505 የነበረው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በአዲሱ በኪሎ ሜትር 0. ነጥብ 554 ተደርጓል፡፡

ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 416 ይከፈልበት የነበረው 0 ነጥብ 039 በኪሎሜትር ጭማሪ በማድረግ 0 ነጥብ 455 በኪሎሜትር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 471 የበነረው በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 049 ጭማሪ በማድረግ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 520 ሆኗል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ ለአንድ ሰው በነባር ታሪፉ በአስፋልት መንገድ ብር 49 ነጥብ 29 ይከፈል የነበረው በአዲሱ ብር 53 ነጥብ 16 ሆኗል፡፡ ይህም በ100 ኪሎ ሜትር ጭማሪ ያደረገው የብር 3 ነጥብ 87 ነው፡፡

በደረጃ ሁለት ተሽከርካሪዎች ለአንድ ሰው በነባር ታሪፍ በ100 ኪሎ ሜትር 45 ነጥብ 70 ያስከፍል የነበረው በ100 በኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 87 በመጨመር 49 ነጥብ 58 በ100 ኪሎ ሜትር ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ በደረጃ ሦስት ተሸርካሪ በ100 ኪሎ ሜትር ለአንድ ሰው ብር 41 ነጥብ 61 ያስከፍል የነበረው በ100 ኪሎ ሜትር የ3 ነጥብ 88 ጭማሪ በማድረግ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 45 ነጥብ 49 ሆኗል መባሉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
14.6K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:00:55 በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድርስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት በነባሩ ክፍያ ታሪፍ በሙሉ አቅም ሊሰሩ ይገባል ተብሏል

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራትና ግለሰቦች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ በነባሩ የክፍያ ታሪፍ መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ የማይሰጡና ህብረተሰቡን ለተለያዩ እንግልቶችና አላስፈላጊ ወጪዎች የሚዳርጉ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በማይገቡትም ላይ ቢሮው አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ቢሮው ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በህጋዊ መንገድ ለተቋሙ ሳያሳውቁ ከስራ ገበታቸው የወጡት የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡስ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት በገቡት ውል መሰረት መብታቸውን እየጠየቁ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስቧል።

የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራቸውን ካቆሙ ቀናት የተቆጠረ ሲሆን ባለንብረቶች በሰጡት ቃል ስራ ያቆሙት ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል ስላልታደሰለቸው እና ተገቢ ክፍያ እየተከፈላቸው ስላልሆነ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
15.6K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 08:23:52
መንግስት ለቀጣዩ ዓመት 780 ቢሊየን ብር በጀት ማዘጋጀቱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ፌዴራል  መንግስት በብርቱ የኢኮኖሚና የፀጥታ ፈተና ውስጥ ሆኖ ከሁለት ወር በኋላ ለሚጀምረው አዲሱ የበጀት ዓመት 780 ቢሊየን ብር በጀት ማዘጋጀቱን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ስምታለች። 

አዲሱ በጀት ካለፈው ዓመት በጀት ጋር ሲነፃፀር የአንድ መቶ ቢሊያን ብር ያህል ብልጫ አለው። የ 2014 ዓ.ም በጀት የአጋማሽ አመቱ ጭማሬ ተዳምሮ 680 ቢሊየን ብር ነበር።

ዘንድሮን በበርካታ መሰናክሎች ያሳለፈው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣዩ ዓመት የበለጠ ፈተና የሚጠብቀው ሲሆን መንግስት አሁን ያሰናዳው 780 ቢሊየን ብር በጀት ከፍ ያለ ጉድለት ሊገጥመው እንደሚችል በበጀት ዝግጅቱ ወቅት በተደረጉ ምክክሮች ላይ መነሳቱን ስምተናል። 

ለ2015 ዓ.ም የተያዘው በጀት ከ 2014 ዓ.ም የ100 ቢሊየን ብር ጭማሬ ይኑረው እንጂ በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሲሰላ ብዙም ለውጥ የሚታይበት አይሆንም።
wazema radio

@Esat_tv1
@Esat_tv1
10.1K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 08:23:41
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
9.8K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 18:06:02
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ። በዚህም መሰረት የ2014 ዓ.ም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 183 ሺህ 500 ብር መሆኑን ምክር ቤቱ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር ያመለክታል።

ምክር ቤቱ የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው የባንክ እና ቁጥሮች ይፋ ያደረገ ሲሆን ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ዋናውን ይዞ መምጣት እንደሚጠበቅበትም ነው ያስታወቀው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
35.0K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 14:05:02 በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል (የሚኒስትሪ) ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተባለ

ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮምኛ ቋንቋዎች ይሰጣል።
ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡በአዲስ አበባ ፣ዝዋይ ፣ሪያድ ጅዳ እና ሱዳን ላይ ባሉ ጣቢያዎቹ የሚገኙ ሰባ አንድ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ አቶ ዲናኦል እንዳብራሩት ከሆነ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል አቶ ዲናኦል ጨምረው ነለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮምኛ ቋንቋዎች እንደሚሰጥም ለማወቅም ችለናል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
45.3K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 11:41:32
የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች በGoogle Translate ሥርዓት ውስጥ ተካተቱ

የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚተረጉመው Google Translate ተጨማሪ 24 ቋንቋዎችን ወደ ሥርዓቱ ማስገባቱን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥም የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች መካተታቸው ተገልጿል።

አዲስ ከተካተቱት ቋንቋዎች ጋር ተደምሮ አገልግሎቱ 133 የዓለም ቋንቋዎችን መተርጎም ያስችለዋል ተብሏል። ከዚህ ቀደም የአማርኛ ቋንቋ በስርዓቱ ውስጥ ተካቶ አገልግሎት ላይ መዋሉ ይታወሳል።

ድርጅቱ ይህንን አገልግሎት ይፋ ያደረገው በትላንትናው ዕለት ሲሆን እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ተደራሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


@Esat_tv1
@Esat_tv1
48.0K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 11:41:29
RIM DICOR

ባሉበት መተን እንሰራለን

ለኒካህ
ልደት
ሰርግ
ቤቢ ሻውር
ምርቃት
ብራይድ

እና ሌሎች ፕሮግራሞች በፈለጋቹት እና በመረጣቹት ዲዛይን እንሰራለን


+251941345081
45.6K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 11:41:09
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
44.1K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ