2022-06-03 19:41:06
የፊታችን ዕሁድ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ
በዚህም መሰረት ፦
ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር (ኦሎፒያ አደባባይ)
ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ በላይና በታች
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ
ከቸርችል ጎዳና በሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፖስታ ቤት
ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር
ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና አካባቢ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር
ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሜክሲኮ አደባባይ
ከሚክሲኮ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር መብራት
ከሰንጋ ተራ በቴሌ ባር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች በድሉ ህንፃ አካባቢ
ከንግድ ማተሚያ ቤት በውስጥ ለውስጥ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦርማ ጋራዥ አካባቢ
ከሸራተን ወደ አምባሳደር ለሚመጡ ፍል ውሃ አካባቢ
ከካዛንቺስ በኩል ወደ ፍል ውሃ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10፡30 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል።
ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት መሰረት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርድ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
31.3K views16:41