Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.66K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 142

2022-06-07 16:17:32
ከሰኔ ወር ጀምሮ በህዝብ ትራንስፖርት ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ

በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ላይ ከ50 ሳንቲም እስከ 3 ብር ከ50 ሳንቲም የሚደርስ ጭማሪ ተደርጓል።

የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እስከ 2.5 ኪሎ ሜትር የሚጓዙ የሚኒባስ ታክሲዎች 50 ሳንቲም የዋጋ ጭማሪ ተደርጎባቸዋል። ከፍተኛ ጭማሪው ደግሞ እስከ 30 ኪሎሜትር ሲሆን ይህም 3 ብር ከ50 ሳንቲም እንዲጨምር ተወስኗል።

የሚዲባስ ወይም ከ30 እስከ 35 ሰው የመጫን አቅም ባላቸው እንደ ሀይገርና ቅጥቅጥ ባሶች ከ50 ሳንቲም እስከ 2 ብር ተጨምሯል የተባለ ሲሆን በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ ምንም አይነት ጭማሪ አልተደረገም።
አዲስ ዘይቤ

@Esat_tv1
@Esat_tv1
49.8K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 12:18:54 ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መዐዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ አዘዘ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ጋዜጠኛ መዐዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት መፍቀዱንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
52.4K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 11:33:57 የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው

የጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የወባ በሽታ፣ ኮቪድ-19 እና የዝንጀሮ ፈንጣጣን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በመግለጫቸው እንዳሉት፥ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ወቅቱ ለወባ በሽታ መዛመት ምቹ ነው።

ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት የሚከሰት መሆኑ ደግሞ ችግሩን የጤና ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ጭምር ያደርገዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
53.6K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 15:54:14
በአዲስአበባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ ነው

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የህግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡ህብረተሰቡም የሚወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቢሮው መልዕክት አስተላልፏል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
36.1K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 12:32:32 በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲ፣ ቢትኮይን እና የመሳሰለው ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ ህገ ወጥ መሆኑን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ

በኢትዮጵያ እንደ ክሪፕቶ ከረንሲ፣ ቢትኮይን እና የመሳሰለው ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን እንዲጠብቅ ባንኩ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ እንደሚደነግግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

በክፍያ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003 መሠረት በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም።

ነገር ግን ከጥናት ለመረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ወቅት ከህግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ፣ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የምናባዊ ንብረት (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል ነው የተባለው።

በተጨማሪም ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል ነው ያለው ባንኩ።

ይህ እየተስተዋለ ያለው ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብን) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል ብሏል ባንኩ።

በመሆኑም ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የገለጸ ሲሆን፥ ህብረተሰቡም ይህንን ህገወጥ ተግባር የሚሠሩ አካላትን ሲመለከት ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን አቅርቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.7K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 12:32:28
በርሶ ፎቶ በፍቅረኛዎ ፎቶ ወይም በሚያደንቁት ሰው ምስል አሳምረን እንሰራለን! ከ ናተ ሚጠበቀው ፎቶውን መላክ ብቻ ነው

ስልክ 0949378569
0918698501

ማሰራት የምትፈልጉ ፎቶአቹን በዚህ Username ላኩልን
@Yaska_yasa
@Smith_Rio

የተሰሩ ሰዓቶችን ለመመልከት

https://t.me/joinchat/AAAAAFGMUgiL2c0_OopkxQ
37.7K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 18:19:19
የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አራት የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ማላዊ ጋር አቻዉ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 - 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አቡበከር ናስር ማስቆጠር ችሏል ። የማላዊውን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ጋባዲንሆ ምህንጎ አስቆጥሯል።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ዋልያዎቹ ያለ ምንም ነጥብ ምድብ አራት ላይ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ሀሙስ ምሽት 1:00 በማላዊ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ ብሄራዊ ቡድን ጋር የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
32.2K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 13:17:14 በፌዴራል ፖሊስ የእውቅናና ምስጋና ምርሀ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና ነጥቦች

የእኛ አላማ ለእውነት የሚሰሩ፣ በእውቀት የሚመሩ ፣ በስነ ምግባር የዳበሩ፣
ሙያቸውን የሚያከብሩ ፣ ለህዝብ የሚኖሩ ፖሊሶችን ለኢትዮጵያ ማበርከት ነው፤

ሰዎች ሁሉ ፀጥ ረጭ ባለው ሌሊት በሰላም ተኝተዋል ምክንያቱም የማይተኙ ሰላም ጠባቂዎች ያለዕንቅልፍ ስለሚያድሩ ነው ይባላል ለዚህ ደግሞ ግንባር ቀደሙ የፌደራል ፖሊስ ነው፤

ሰላም እፈልጋለሁ ችግር የሚመጣ ከሆነ ግን በእኔ ዘመን እንዲመጣ እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም የእኔ ልጆች በሰላም እንዲኖሩ ስለምፈልግ የሚባለው አባባል በትክክል የሚሰራው ለኢትዮጵያ ፖሊስ ነው፤

የኢትዮጵያ ፖሊስ በጎችን ከተኩላዎች ለመጠበቅ 24 ሰአት የሚሰራ ሃይል ነው፤ ብዙ ተኩላዎች ሲጮሁ ይሰማል፤ የጩኸቱ ትርጉም በጎችን እንደፈለግነው እንብላ ተዉን ነው፤ ፖሊሶች ከተኩላዎች ምስጋና አይገኝምና ስራችሁን አጠናክራችሁ እንደትቀጥሉ እላለሁ ፤ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ ሃይሎች ይፈርሳሉ፤

ኢትዮጵያ ህልውናዋና ሉአላዊነቷ ለአደጋ በተጋለጠ ጊዜ ሁሉ ፖሊስ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ነውና ክብር ይገባዋል፤ እናንተ የሰላም ዘቦች የብርሃን ጥቅም የሚታወቀው ጨለማ በሚሆበን ወቅት እንደ ሆነ ሁሉ የህግ አስከባሪዎች ሚና የሚታየውም ሰላምና ደህንነታችን አደጋ ሲወድቅ ነው፤

የሰላምን ዋጋ ብንገነዘብ ላፍታም ቢሆን ወደ ግጭት አናመራም ሰዎች ወደ መከራ ወደ ግጭት ሲገቡ የሰላም አስፈላጊነትን የሚገነዘቡ ቢሆንም የሰላም ዋጋ የረከሰ በመሆኑ ለእናንተ ሚናና ጥረት እምብዛም ክብር ያልሰጠን ቢሆንም ተኝተን የምናድረው ፣ አርሰን የምንበላው፣ ሀገራችን ለማበልፀግ የምንጥረው እናንተን ተማምነን ነው፤

በፖሊሶች የከሸፉ ወንጀሎችን ሳይሆን ከፖሊስ ዕይታ ያመለጡ ወንጀሎችን አግዝፎ የሚመለከት ባህል አለን፤ በየዘመናቱ፣ በየጊዜያቱና ቀናቱ ፖሊስ ለእኛ የማይነግረንን ብዙ ወንጆሎችን ያከሽፋል፤ ነገር ግን ያከሸፈውን የለፋበትንና መሰዋዕትነት የከፈለበትን ሳይሆን አልፎ አልፎ ከፒሊስ ዕይታ ያመለጠውን አብዝተን እንናገራለን፤

ፀጥታና ሰላማችንን ለማረጋጋጥ ሲዋደቁ ያላከበርናቸውን ፖሊሶች ወንጀል ሲፈፀምብን ጣታችን ልንቀስርባቸውና ልንወቅሳቸው አይገባም፤ ኢትዮጵያ በእጅጉ ለሚያገለግሏት ፖሊሶች በቂ ደሞዝ መክፈል ባትችልም እንኳን ማክበር መለማመድ ይኖርባታል፤

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለችላቸው ያስተማረቻቸው ከምንም ወደ ገዘፈ ማንነት ያደረሰቻቸው ግለሰቦች የፖሊስን ግማሽ ዋጋ ቢከፍሉ ኢትዮጵያችን ምን ልትሆን እንደምትችል ላፍታ እንድታሰቡ እጠይቃለሁ።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
42.9K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 11:08:03
የፖሊስ አመራርና አባላት የእውቅና እና የምስጋና አሰጣጥ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻዎች እንዲሁም በፖሊሳዊ ሥራዎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራርና አባላት የእውቅና እና የምስጋና አሰጣጥ መርኃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ዋና ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ፣ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ተገኝተዋል።

"በመስዋትነታችን የሀገራችን አንድነት የሕዝባችን ሰላም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለውን መርኃ ግብር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየታደሙ ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
45.0K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 22:43:16
አቶ ጃዋር መሐመድ በእስር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ለሳቸው እና አብረዋቸው ለታሰሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ደጋፊዎቻቸው አድርገዋል ላሉት ጥረት ዛሬ ምስጋና አቀረቡ

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አቶ ጃዋር መሐመድ ምስጋናውን ያቀረቡት ዛሬ በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አቅራቢያ በተዘጋጀ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በአካል ተገኝተው ነው። ይህ የጉዟቸው አንደኛው አላማ ሲሆን ሌላኛዋ አላማ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚደረግ ጥረት ውስጥ ደጋፊዎቻቸው የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማሳሰብ ነው ተብሏል።

ጉብኝታቸው አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካን የሚያካልል ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ እና ቤልጄም ከመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት ከደጋፊዎቻቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀኑ ዶይቸ ቬለ ዘግቧል።

አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ለሁለት ዓመት ገደማ ያህል በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
15.0K views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ