Get Mystery Box with random crypto!

ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መዐዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በ10 ሺህ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መዐዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ አዘዘ

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ጋዜጠኛ መዐዛ መሀመድ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት መፍቀዱንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1