Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.66K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 144

2022-06-02 14:00:17 ለአሸባሪው ህወሃት ከ800 ሺህ ብር በላይ ሊያስተላልፉ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ለአሸባሪው ህወሃት ከ800 ሺህ ብር በላይ የሆነ ጥሬ ገንዘብ ሊያደርሱ የነበሩ 11 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ተገኘ ወርቁ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በህገ ወጥ መንገድ ለአሸባሪው ህወሃት ጥሬ ገንዘብ ለማስተላለፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመግታት ክትትል እየተደረገ ነው።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ባለፉት ሶስት ቀናት ለአሸባሪው ቡድን ሊተላለፍ የነበረ 804 ሺህ 260 ብር ከነተጠርጣሪ አዘዋዋሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልፀዋል።

ከተያዘው ጥሬ ገንዘብ ውስጥ 594 ሺህ 260 ብር ያህሉ ትናንት ሌሊት በባጃጅና በባለ አንድ ጋቢና ቶዮታ መኪና በኬሻ ተሸፍኖ ሊያልፍ ሲል በፀጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮማንደር ተገኘ ጠቁመዋል።

በህገ ወጥ መልኩ ለሽብር ቡድኑ ጥሬ ገንዘቡን ለማድስተላለፍ በመሞከር ወንጀል የተጠረጠሩ 11 ግለሰቦችና አንድ ባጃጅ በህግ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የህገ ወጥ ንግድንና የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ህብረሰተሰቡ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በወረዳው የሌሊት ጉዞ የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ኮማንደር ተገኘ ጥሪ አቅርበዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
43.9K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 11:17:21
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገባ

በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው። የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
48.5K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 11:17:16
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
46.7K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 21:32:21
ከዛሬ ጀምሮ የሲሚንቶ ግብዓትና ምርት ስርጭትን በሚያስተጓጉሉ ህገ-ወጦች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዱና የመዓድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ታከለ ኡማ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዱ በመግለጫቸው፤ በክልሉ በሲሚንቶ ምርት ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የሚያስችል እርምጃ ክልሉ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።

በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች በሚገኙ ያልተገባ ክፍያ በመጠየቅ የግብዓትና ምርት ስርጭት ላይ እንቅፋት የሆኑ ኬላዎችን በማንሳት ግብዓቱ በቀጥታ ወደ ፋብሪካዎች የሚደርስበት አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

አክለውም ምርቱ ከፋብሪካዎች በ400 ብር እና በ500 ብር የሚወጣ ቢሆንም በርካታ ደላሎች በመሀል የምርቱን ዋጋ እስከ 1 ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ማድረጋቸው በመግለጫው ተነስቷል። በመሆኑም ክፍተቶችን በመፈተሽ ህጋዊ ማኅበራትን በማደራጀት የምርት ስርጭቱ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው የሚደርስበትን አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።

ከአምራች እንደስትሪዎች ጋር በተገናኘ የሚነሱ የፀጥታና የግብዓት ችግሮች ለመቅረፍ ክልሉ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑና ችግሩንም ለመቅረፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
23.0K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:28:26 ፌደራል ፖሊስ ህገ-ወጥ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ህገ-ወጥ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የፌደራል ፖሊስ በመግለጫው እንዳስታወቀው፡- ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል ብሏል።

የፌደራል ፖሊስ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ህገ-ወጥ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ፡-

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/ 2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል።

ከዚህ ውስጥ በጣም ወጣ ያሉ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱትን ለይቶ 10 (አስር) ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው ይገኛል።

እነዚህ ግለሰቦች የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት እንዳይረጋጋ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በብሄር እና በሀይማኖት መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲያደርጉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል።

ተቋሙ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸውና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ያልተመዘገቡ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል። ግለሰቦቹ የሚዲያ ተከታዮቻቸውን በመጠቀም ሐሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን የሚያሰራጩት በክፍያ እንደሆነም በምርመራ ደርሶበታል።

በየትኛውም ሚዲያ ተጠቅመው መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ ግለሰቦች የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት አክብረው መንቀሳቀስ እና ህጋዊ መስመር በመከተል በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል። ፖሊስም ህግን አክብረው በማይሰሩት ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ ይወዳል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ያገኛውን መረጃ ሁሉ ከመጠቀም በመቆጠብ በጥንቃቄ መርምሮ ማየትና ማገናዘብ እንዳለበት እያሳሰበ በህግ-ወጥ መንገድ በበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት አጀንዳ ቀርፀው በሀይማኖት፣ በብሄር ህብረተሰቡን ለማጋጨት የሚሰሩ አከላትን በማጋለጥና ለህግ አሳልፎ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ለህዝብ ሲገለጽ እንደነበረው ከሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
37.5K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 14:07:02
በአማራ ክልል ተያዙ ከተባሉት ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት እገታና አግባብ የሌለው እስር መሆኑን ኢሰመጉ ገለፀ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በአማራ ክልል በህግ ማስከበር ስም ከታሰሩት ከ4 ሺህ 500 በላይ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የተወሰኑት በህግ አግባብ ያልተያዙ ናቸው አለ።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከግንቦት 2014 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት ህግ ማስከበር ዘመቻ በሚል ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መግለጹ የሚታወስ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ኢሰመጉ ባሰባሰባቸው መረጃዎች በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ እስሮች ተገቢውን የህግ ስነስርአት ያልተከተሉ እና እገታም የታከለባቸው መሆናቸውን መረዳቱን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዚህ ሂደት በተፈጠሩ ግጭቶች እና በተወሰዱ እርምጃዎች በክልሉ በሚገኙ አካባቢዎች የ13 አመት ታዳጊን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት፣ እስራት እና እገታ መፈጸሙን ኢሰመጉ ከአካባቢዎቹ ባሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳቱንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ በጋዜጠኞች፣በተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እና በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ህገወጥ እስር እና እገታ እየተፈጸመ በመሆኑ መንግስት የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ሲጠይቅ መቆየቱን በማስታወስ አሁንም ሕገወጥ እርምጃው በመንግስት በኩል እንደቀጠለ ነው ብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
47.8K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 14:06:58
በርሶ ፎቶ በፍቅረኛዎ ፎቶ ወይም በሚያደንቁት ሰው ምስል አሳምረን እንሰራለን! ከ ናተ ሚጠበቀው ፎቶውን መላክ ብቻ ነው

ስልክ 0949378569
0918698501

ማሰራት የምትፈልጉ ፎቶአቹን በዚህ Username ላኩልን
@Yaska_yasa
@Smith_Rio

የተሰሩ ሰዓቶችን ለመመልከት

https://t.me/joinchat/AAAAAFGMUgiL2c0_OopkxQ
44.3K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 14:06:45
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
43.9K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 18:31:35
ኦባሳንጆ በመቀሌ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ጋር ተወያዩ

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡ቃል አቀባዩ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ኦባሳንጆን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

“በቀጠናዊ ጉዳዮች” ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል ቃል አቀባዩ፡፡ ሆኖም ”ቀጣናዊ” የተባለው ጉዳይ ምን እንደሆነ አቶ ጌታቸው በግልጽ አላስቀመጡም፡፡ የተወያዩባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እንዳሉም አልገለጹም፡፡የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የመቀሌ ጉዞ በተመለከተ የፌዴራል መንግስቱ የሰጠው መግለጫም ሆነ ያለው ነገር የለም፡፡
Alain

@Esat_tv1
@Esat_tv1
35.9K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 11:04:47
የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ህወሃት " የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ " በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም አሉ

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ነው።

ዶ/ር ለገሰ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት ነው ፤ የተመቱትም ራሳቸው የህወሃት ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

በኤርትራና በህወሃት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው እራሱ ህወሃት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ ሁኔታ ህወሃቶች " ሬሳ እንኳን መንሳት አልቻሉም፤ በጣም ብዙ ሰው ወድሞባቸዋል "ሲሉ ተናግረዋል።

በህወሃትና በኤርትራ መካከል ያለው መካረርና አልፎ አልፎ እየተደረገ ያለው ውጊያ ፤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ወደጦርነት ሊያስገባ አይችልም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ " ወደዚያ የሚያመራ ሁኔታ የለም " ሲሉ ተናግረዋል

ህወሃት ትንኮሰውን የሚፈፅመው ሁለቱን ሀገራት ወደ ግጭት ለማስገባት እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር ለገሰ " ይህ መቼም ቢሆን አይሳከም " ብለዋል፡፡

መንግስት በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መረጃ እንዳለው ገልፀው፡ ህወሃት ኤርትራ እና ኢትዮጵያን ለማጋጨት እየሰራ ቢሆንም ሁለቱ ሀገራት መቸም ቢሆን ወደ ግጭት አይገቡም ሲሉ ለአልዓይን ተናግረዋል።

ትላንት ህወሓት ባሰራጨው መረጃ ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር እንዲሁም ከ4 ቀን በፊት በአዲአዋላ ውጊያ መደረጉን አሳውቆ ነበር።

በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና 3 የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮች እንደተገደሉ 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና 4 ወታደሮች እንደተማረኩ ገልጿል። 1 ድሽቃ፣ 5 የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም መገለፁ አይዘነጋም።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
51.2K views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ