Get Mystery Box with random crypto!

ኦባሳንጆ በመቀሌ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ጋር ተወያዩ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

ኦባሳንጆ በመቀሌ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ጋር ተወያዩ

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡ቃል አቀባዩ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ኦባሳንጆን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

“በቀጠናዊ ጉዳዮች” ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል ቃል አቀባዩ፡፡ ሆኖም ”ቀጣናዊ” የተባለው ጉዳይ ምን እንደሆነ አቶ ጌታቸው በግልጽ አላስቀመጡም፡፡ የተወያዩባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እንዳሉም አልገለጹም፡፡የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት የመቀሌ ጉዞ በተመለከተ የፌዴራል መንግስቱ የሰጠው መግለጫም ሆነ ያለው ነገር የለም፡፡
Alain

@Esat_tv1
@Esat_tv1