Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯን አለማቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ነው፡፡

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።

ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1