Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ብ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የአማራ ክልል ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ይቅርታውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ የይቅርታ አሠጣጥ መመሪያዎች መሠረት በበጀት አመቱ ሁለተኛ ዙር በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አንስተዋል።

በይቅርታው በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በመታረምና በመታነፅ አርአያነት ያሳዩ፣ ከተበዳይ ወገኖች ጋር እርቅ የፈፀሙ፣ አስፈላጊውን ካሳ የከፈሉ እና ለማህበረሠቡ የወንጀልን አስከፊነት እንደሚያስተምሩ የታመነባቸው 1 ሺህ 431 ወንድ እንዲሁም 29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ገልፀዋል።

በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ የተሠጣቸውን ይቅርታ ባለመጠበቅ ሌላ ወንጀል ፈፅመው በቻግኒ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አምስት ግለሠቦችን ይቅርታ መሰረዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

የህግ የበላይነት የሁለንተናዊ ለውጥ እና ለዘላቂ ሠላም መሠረት ነው ያሉት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚታየው የፀጥታ ችግርና በሌሎችም አጋጣሚዎች ከማረሚያ ቤት የወጡ ፍርደኞች እና ጉዳያቸው በሂደት ላይ የነበሩ ታራሚዎች ተመልሠው በህግ እንደሚዳኙም ገልፀዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1