Get Mystery Box with random crypto!

የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ

መሰረታቸውን በዉጪ ያደረጉ ባለሃብቶች በችርቻሮ እና በጅምላ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አስታውቀዋል።

ከጅምላ ንግድ ጋር ተያይዞ ከማዳበሪያና ከነዳጅ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል በዚህም በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ነዉ የተፈቀደው ።

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች አሁን ደግሞ ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1