Get Mystery Box with random crypto!

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሰርጥ አድራሻ: @esat_tv1
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 246.66K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 145

2022-05-31 10:09:51
በደሴ በተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

በደሴ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ አራዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በድርጅትና መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ ገለጸ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ጥላሁን ፈንታው ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ ከለሊቱ 6 ሰዓት ገደማ የተቀሰቀሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ርብርብ ሲያደርጉ በነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት አስከትሏል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሰዓቱ ወደ ህክምና ተቋም ሄደው እርዳታ እንዲያገኙ እንደተደረገም ተናግረዋል።“የእሳት አደጋው የተነሳበት አካባቢ አሮጌ እቃዎች የሚከማቹበትና ያረጁ ቤቶች ያሉበት በመሆኑ በቀላሉ ለማጥፋት ፈታኝ ቢሆንም በህብረተሰቡ ርብርብ እሳቱ ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏል” ብለዋል፡፡የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሸከርካሪ ከኮምቦልቻ ከተማ ጭምር መጥቶ ለማጥፋት ርብርብ መደረጉን ጠቁመው ፥ በቅንጅት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።የአደጋው መንስኤ፣ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት፣ የተቃጠሉ ቤቶችና ሌሎችንም የሚያጣራ ቡድን ወደ ቦታው ተልኮ ስራ መጀመሩን ኃላፊው ተናግረዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
48.2K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 10:09:47
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+x8RIy5m4HlxiNGRk
46.2K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:04:42
በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ

ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ ተወስኗል ነው የተባለው፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
23.6K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 16:13:52
የተባበሩት መንግሥታት ሀገራዊ ምክክሩን በመደገፍ ከመንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገለጸ

ሀገራዊ ምክክሩ በሰላም ግንባታው ላይ የሚኖረውን አዎንታዊ ተፅዕኖ በመደገፍ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴክን ተናገሩ፡፡

የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴክን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሀገራዊ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሥራዎች፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እየተደረገ ስለሚገኘው ሰብዓዊ ድጋፍና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነው ውይይት ያደረጉት፡፡

ልዩ መልዕክተኛዋ ለትግራይ ክልል ሕዝብ እየቀረበ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ መልካም የሚባል መሆኑን ገልጸው መንግሥት ለሰብዓዊ ድጋፉ ያሳየው ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በሌሎች ክልሎችም በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገውን ሰብዓዊ ድጋፍ በማገዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንሰራለን ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሂደት በመደገፍና በቀጣይ የሚደረገውን አካታች ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ ለማድረግና ሀገራዊ ምክክሩ በሰላም ግንባታው ላይ የሚኖረውን አዎንታዊ ተፅዕኖ በመደገፍ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
41.7K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:17:42
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባውን የኩላሊት እጥበት ማዕከል መረቁ

በምረቃው መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል።

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊና ብቁ የጤና ተቋማት በመገንባት ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው መገለጹን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
50.0K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 21:29:37 በሳምንት ለ240 ሺህ ዜጎች አገልግሎት የሚሰጠው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ስራ ጀመረ

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና በሳምንት ለ240 ሺህ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ማእከሉ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም አቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው።

በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማእከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎችም በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ነው የተገለፀው።

በሳምንት 240 ሺህ ዜጎች የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉበት ማዕከሉ በነገው እለት እንደሚመረቅም ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/በት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
20.6K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 16:59:06
በመዲናዋ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነው

በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰቶችን በተሻለ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ።

የህዝቡ ተሳትፎ ማነስ፣ የአንዳንድ ደንብ ተቆጣጣሪዎች የግንዛቤ ማነስና የሥነ ምግባር መጓደል እንዲሁም የአንዳንድ አስፈፃሚ አካላት ጣልቃ ገብነት ለደንብ ማስከበር በችግርነት ከሚነሱት መካከል እንደሚጠቀሱ ተገልጿል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ፉፋ፤ የደንብ መተላለፍ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የአሠራር ሥርአት መዘርጋት ማስፈለጉን ገልጸዋል።

የመሬት ወረራ፣ ህገ ወጥ ግንባታ፣ የጎዳና ላይ ንግድን ጨምሮ ሌሎችንም ለመከላከልና ለመቆጣጠር የደንቡ መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑንም አብራርተዋል።

በሰው ኃይል እስከ ታችኛው እርከን በባለሥልጣኑ አዲስ አደረጃጀት ተሠርቶ መጠናቀቁን ጠቁመው ይህም የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያግዛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
39.1K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:55:04
ናሚቢያ በነዳጁ ዘርፍ የአዉሮጳ ህብረትን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች

የአውሮጳ ህብረት ከሩሲያ በነዳጅና በጋዝ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማቆም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ለዚህም ደቡብ አፍሪቃዊትዋ  ሀገር ናሚቢያ በነዳጁ ዘርፍ የአዉሮጳ ህብረትን እኔ መርዳት እችላለሁ እያለች ነዉ።

ናሚቢያ ይህን ያሳወቀችዉ ባለፈው ሳምንት ዳቮስ ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ዓመታዊ የኤኮኖሚ መድረክ ላይ ሲሆን ልረዳ እችላለሁ ብላ የቀረበች የመጀመርያዋ ሃገርም ተብላለች።

ናሚቢያ ከምትሸጣቸዉ ሀብቶችዋ መካከል የፀሐይ ብርሃን እና የንፋስ ኃይል ይገኝበታል። በዓመት ከሦስት ሺህ ሰዓት በላይ የፀሀይ ብርኃን ከሚገኝባቸዉ የዓለማችን ደረቅ ሀገራት መካከል ናሚቢያ አንዷ ናት። 

ናሚቢያ ፀሐይና ነፋስን በመጠቀም ከባሕር ውኃ ውስጥ እንደ ኤሌትሪክ ኃይል የሚሰጠዉን አረንጓዴ ሃይድሮጂን ፕሮጀክት ለመሥራት ያሰበች ሲሆን ፕሮጀክቱ ውሎ አድሮ በየዓመቱ እስከ 300,000 ቶን የሚደርስ አረንጓዴ ሃይድሮጅን የሃይል ምንጭ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።

የአውሮጳ ህብረትም ከከርሰ ምድር የሚገኝ ነዳጅ ላይ ያለውን ፍላጎት እና ጥገኝነት በመቀነስ ከባሕር ውኃ ውስጥ የሚገኝ አረንጓዴ ሃይድሮጅን የተባለ ለከባቢ አየር ጥራት እጅግ ምቹ የሆነ የኃይል ማመንጫ እየፈለገ መሆኑን አሳዉቋል። 
DW

@Esat_tv1
@Esat_tv1
46.2K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 16:08:00
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ

ከቀናት በፊት በተደረገው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ዳግም መመረጥ የተቃወመችው ኢትዮጵያ ከግንቦት 14 2014 ዓ.ም ጀምሮ በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል አድርጋ አስመርጣለች።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 34 በጤና ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው እና በአባል ሀገራት የተወከሉ ባለምያዎችን በሚይዘው ቦርድ ውስጥ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት ሀገራት ተወካዮቻቸውን ያስመረጡ ሲሆን እነኚህ ተመራጮች ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ድርጅቱን ያገለግላሉ። የቦርዱ ዋነኛ ተግባር የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ እና ፖሊሲ ማስፈጸም እንዲሁም ምክረ-ሀሳብ ማቅረብ እና ስራዎችን ማመቻቸት ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
41.1K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 12:40:33
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተያዘች

"ሮሃ ሚዲያ" የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋን ዋቢ አድርጎ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " ዘግቧል።

የጋዜጠኛዋ እስር በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 አድርሶታል።

ጋዜጠኛ መዓዛ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ 2 ፖሊሶች እና የሲቪል ልብስ ባደረጉ 3 የጸጥታ ኃይሎች የተያዘችው በአዲስ አበባ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከሚገኝ የእርሷ መኖሪያ ቤት እንደሆነ ጋዜጠኛ ምስራቅ ተፈራ ገልጻለች።

የጸጥታ ኃይሎቹ መዓዛን ለ " ጥያቄ እንፈልጋታለን " በሚል ምክንያት ቢይዟትም ወዴት እንደሚወስዷት ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ጋዜጠኛዋ ማስረዳቷን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል። ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ከወራት በፊት ለእስር ተዳርጋ መፈታቷ ይታወሳል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
47.2K views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ