Get Mystery Box with random crypto!

የተባበሩት መንግሥታት ሀገራዊ ምክክሩን በመደገፍ ከመንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገለጸ ሀገራ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የተባበሩት መንግሥታት ሀገራዊ ምክክሩን በመደገፍ ከመንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገለጸ

ሀገራዊ ምክክሩ በሰላም ግንባታው ላይ የሚኖረውን አዎንታዊ ተፅዕኖ በመደገፍ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴክን ተናገሩ፡፡

የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴቴክን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሀገራዊ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሥራዎች፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እየተደረገ ስለሚገኘው ሰብዓዊ ድጋፍና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነው ውይይት ያደረጉት፡፡

ልዩ መልዕክተኛዋ ለትግራይ ክልል ሕዝብ እየቀረበ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ መልካም የሚባል መሆኑን ገልጸው መንግሥት ለሰብዓዊ ድጋፉ ያሳየው ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በሌሎች ክልሎችም በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገውን ሰብዓዊ ድጋፍ በማገዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንሰራለን ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሂደት በመደገፍና በቀጣይ የሚደረገውን አካታች ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ ለማድረግና ሀገራዊ ምክክሩ በሰላም ግንባታው ላይ የሚኖረውን አዎንታዊ ተፅዕኖ በመደገፍ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1