Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነው በአዲ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በመዲናዋ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነው

በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰቶችን በተሻለ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ።

የህዝቡ ተሳትፎ ማነስ፣ የአንዳንድ ደንብ ተቆጣጣሪዎች የግንዛቤ ማነስና የሥነ ምግባር መጓደል እንዲሁም የአንዳንድ አስፈፃሚ አካላት ጣልቃ ገብነት ለደንብ ማስከበር በችግርነት ከሚነሱት መካከል እንደሚጠቀሱ ተገልጿል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ፉፋ፤ የደንብ መተላለፍ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የአሠራር ሥርአት መዘርጋት ማስፈለጉን ገልጸዋል።

የመሬት ወረራ፣ ህገ ወጥ ግንባታ፣ የጎዳና ላይ ንግድን ጨምሮ ሌሎችንም ለመከላከልና ለመቆጣጠር የደንቡ መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑንም አብራርተዋል።

በሰው ኃይል እስከ ታችኛው እርከን በባለሥልጣኑ አዲስ አደረጃጀት ተሠርቶ መጠናቀቁን ጠቁመው ይህም የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያግዛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1