Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት መካከል የ19 ሚሊዮን ዩሮ የዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ በኢትየ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት መካከል የ19 ሚሊዮን ዩሮ የዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ

በኢትየዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ ሦስት የተለያዩ ፕሮጀክቶች የፈረንሳይ መንግስታት 19 ሚሊየን ዩሮ ወይንም 1 ነጥብ 02 ቢሊየን ብር ዕርዳታ ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የዕርዳታ ስምምነት አድርጓል።

የመጀመሪያው ፕሮጀክት የ 8 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች ለመጠገንና ለመንከባከብ የሚያስችል ሲሆን ቅርሶቹ ለቱሪስቶችና ለጎብኝዎች በሚያመች መልኩ ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው፡፡

ሁለተኛው ፕሮጀክት የ10 ሚለየን ዩሮ ድጋፍ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሀይልን የሰራተኛውን ክህሎት በማሳደግ የተቋሙን ውጤታማነትን ለማጠናከርና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚያግዝ ነው፡፡

ይህን ለማድረግ እንዲቻል የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያስገነባውን የስልጠና ተቋም ግንባታና የውስጥ መገልገያ መሳሪያዎች ለማሟላትም የሚውል የፕሮጀክት ድጋፍ ነው፡፡

ሶስተኛው ፕሮጀክት የአንድ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ሲሆን በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራትን ኤጀንሲን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የሲቪል ማህበራትን አቅም በመገንባትና በማጠናከር ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያግዛቸው ነው፡፡

ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰውና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ መንግስት ልማት ድርጅት ሀላፊ ቫሌሪ ቲአዎ የፈረንሳይ አምባሳደር በኢትዮጵያ ሬሚ ማስቹዌክስ በተገኙበት መፈረማቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1