Get Mystery Box with random crypto!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር የፈረመቻቸውን ስምምነቶች እና የ | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር የፈረመቻቸውን ስምምነቶች እና የፋይናንስ ድጋፍ ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮልን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2013 ዓ፣ም ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር የፈረመቻቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት፣ የወታደራዊ ፋይናንስ ስምምነት እና የፋይናንስ ድጋፍ ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮል ዛሬ ማጽደቁን የዋዜማ ሪፖርተር ዘግባለች።

የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነቱ በወታደራዊ ልምምዶች፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ በወታደራዊ መረጃ፣ ልውውጥ፣ በወታደራዊ ኮምንኬሽን ወዘተ የሁለትዮሽ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ነው።

የወታደራዊ ፋይናንስ ስምምነቱ ደሞ ኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት ቱርክ ሰራሽ የመከላከያ መሳሪያዎችን ከቱርክ ኩባንያዎች እንድትገዛና ያለ ቱርክ ፍቃድ መሳሪያዎቹን ለሦስተኛ ወገን አሳልፋ እንዳትሰጥ የሚከለክል ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1