Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀም | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የአማራ ክልል ዜጎች የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ

ከግንቦት 9/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል።

የቢሮው ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፤ የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አሸባሪው ትሕነግ የጥፋት መንገድ ተጋሪዎች የአማራን ሕዝብ አንድነት ለመሸርሸር በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን የተለያዩ አጀንዳዎችን እየዘረጉ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው የሽብር ቡድኑ አሁንም ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው ብለዋል።

የጥፋት ኃይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1