2024-04-09 22:30:15
በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው አፈሳ እና የታሰሩ ሰዎችን ለማስለቀቅ በገንዘብ የሚደረግ ድርድር
ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በከተማው 'ወቅታዊ' በሚል ምክንያት ከፍተኛ አፈሳ እየተፈፀመ እንደሆነ፣ በዚህም በርካታ ግለሰቦች ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ እንደሆነ የሚደርሱኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።
እስሩ በብዛት የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ፣ ከሬስቶራንት፣ መዝናኛ ስፍራዎች እና የስራ ቦታ ጭምር አፈሳው እየተፈፀመ እንደሆነ ምንጮች የጠቆሙኝ ሲሆን ጉዳዩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ደርሶ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነም ታውቋል።
አፈሳውን በአብዛኛው የሚፈፅሙት ሲቪል የለበሱ 'ክትትል' የሚባሉ አካላት ሲሆን ለምሳሌ 22 አካባቢ አደይ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው ፖሊስ ጣብያ አይነት ማቆያዎች ለዚህ ተግባር እየዋሉ እንደሆኑ እና ከሞሉ ደግሞ ኮንቴይነሮች ውስጥ እንዲታሰሩ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል።
ታዲያ ይህን እስር ለየት የሚያደርገው አንዳንድ የፀጥታ አካላት በግልፅ የገንዘብ ድርድር በማድረግ ታሳሪዎችን በገንዘብ መልቀቃቸው ነው፣ ከ30,000 ብር እስከ 80,000 ብር ያውም በግልፅ በባንክ ትራንስፈር እንደሚደረግ ታውቋል።
በርካታ ምስጉን የፀጥታ አካል እንዳሉ ብናውቅም እንዲህ አይነት በጫካ ከሚደረግ እገታ ያልተናነሰ ወንጀል መሀል ከተማ እንደሚፈፀም መንግስት መረጃው ይኖረው ይሆን?
@EliasMeseret
30.0K viewsElias M, 19:30