2023-02-20 21:35:41
#UPDATE በ3.8 ቢሊየን ብር ወጪ ግዢ ስለተፈፀመባቸው 200 ባሶች እና አነጋጋሪ ዋጋቸው ከአራት ቀን በፊት አንድ መረጃ አጋርቼ ነበር፣ በዚህ ዙርያ ማብራርያ ሊሰጥ እንደሚገባም ሀሳብ ሰንዝሬ ነበር።
ለማስታወስ ያህል: ከላይ በተጠቀሰው ስሌት መሰረት አንዱ አውቶቡስ የተገዛው 19 ሚልዮን ብር (ወይም 354,000 ዶላር ገደማ) እንደሆነ፣ ነገር ግን እኔ በግሌ ሁለት የቻይና መኪና አቅራቢ ድርጅቶችን አናግሬ ዋጋቸው ከ111,000- 130,000 ዶላር ገደማ እንደሆነ እንዳሳወቁኝ ፅፌ ነበር።
በዚህ ዙርያ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ጉዳዩን ያስረዳሉ ያሏቸውን ነጥቦች በስፋት አብራርተውልኛል። አቶ ምትኩ ያነሱልኝን ነጥቦች ሳልጨምር፣ ሳልቀንስ አቅርቤው አንባቢ የራሱን ግንዛቤ ይውሰድ:
- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በኩል የ200 ባስ ግዥ ተፈፅሟል። የ200 ባስ ግዥ ጨረታ ሰነዱ የቀረበው የተለያዩ ወጭዎችን ሸፍኖ ማለትም የዉጭ መንዛሬም ሆነ ለሎች ነገሮችን አጠቃሎ በአድራሻችን ማቅረብ ነበር።
- ለዚህ ግዢ ያደታ ጁነይዲ (የ Higer Bus አቅራቢው) በአነስተኛ ዋጋ አሸንፏል፣ ዋጋውም ወደ 18.9 ሚልዮን ብር ገደማ ነበር። ሁለተኛ የሆነው ድርጅት ያቀረበው 22 ሚልዮን ብር ገደማ ነበር። ይህ ግዢ በአመት ለድጋፍ ሰጪ ባሶች ከከተማ አስተዳደሩ የሚከፈለውን 600 ሚልዮን ብር አስቀርቶ ወደፊት ሌሎች ባሶችን ለመግዛት ታሳቢ ያረገ ነበር።
ዋጋው ከአውቶብሱ የታች መሸጫ ዋጋ (base price) ለምን እጅግ ከፍ ያለ ሆነ የሚለውን ጥያቄዬን ሲያብራሩ:
1ኛ: የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላለ አውቶብሶቹ የተገዙት በውጭ ምንዛሬ ሳይሆን በብር ነበር (አቅራቢው ድርጅት ዶላር በራሱ አቅርቦ)። ያናገርናቸው አንዳንድ የቻይና ኩባንያዎች ጭራሽ በዶላር እንጂ በብር ግብይት አንፈፅም ብለዋል።
2ኛ: አውቶብሶቹ የተገዙት በቀጥታ ከፋብሪካው/አምራቹ ሳይሆን ከመኪና አቅራቢ ድርጅት፣ ይህም መሀል ላይ ያለ የድርጅት ትርፍን ታሳቢ ያደረገ ነበር።
3ኛ: አውቶብሶቹ በተለያየ ማዘመኛ ስፔክ (specifications) የተገጠመላቸው ናቸው። ከቻሲስ ስር ያሉ ዋና ዋና ክፍሎቹ ከጀርመን በመጡ ምርቶች እንዲደረጉ አስደርገናል፣ ይህም ዋጋው ላይ ጭማሬ አስከትሏል።
4ኛ: እንደ ሱር ታክስ፣ ዊዝሆልዲንግ እና ቫት ያሉ ቀረጦች ተጨምረውበታል፣ ይህም ወደ 30 ፐርሰን ይደርሳል። ግዢው በዚህ መልኩ ቢፈፀምም ወደፊት እኛ ከገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን መልሰን እንጠይቃለን (ወደኋላ ተመላሽ ይሆናል)።
5ኛ: ከዛም የማስጫኛ፣ የወደብ ክፍያ፣ ኢንሹራንስ፣ ዲመሬጅ... ወዘተ ክፍያዎች ነበሩበት።
-------------------------------------------------------------
*እንደ ማንኛውም የሚድያ ስራ ሁሉንም ባላንስ ማረግ እና እኩል ቦታ መስጠት ተገቢነት እንዳለው አምናለሁ። በመግቢያው እንዳልኩት አንባቢዎች የራሳቸውን ንፅፅር አድርገው ግንዛቤ ይውሰዱ፣ በዚህ ገለፃ ለእኔ አንዳንድ መልሶችን ባገኝም አሁንም ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች እንዳሉ አሉ። ጉዳዩን ለኔ ለማስረዳት ርቀት ለሄዱት የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ግን ምስጋና
መልካም ምሽት!
@EliasMeseret
24.8K views18:35