Get Mystery Box with random crypto!

በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።

ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት አቶ ሙሄ ፣ልጃቸው አበባዉ ሙሄ፣ ሽኩር ሙሄ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን "ሀሩን ሚዲያ" ዘግቧል።

እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

Via Tikvah Ethiopia

@EliasMeseret