Get Mystery Box with random crypto!

የህግ ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ ወዳጄ የሆነው ጠበቃ ሙሉጌታ በላይ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ እያወጣ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የህግ ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ ወዳጄ የሆነው ጠበቃ ሙሉጌታ በላይ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ እያወጣ ያለውን የተጠርጣሪዎች ፎቶ በተመለከተ ይህን ብሏል። ቪድዮው ሲጠቃለል:

- የግለሰቦችን ምስል ለህዝብ ማውጣት በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸው ፖሊስ እና ፍርድ ቤት ብቻ ናቸው

- ባንኩ ማድረግ የሚችለው በእነዚህ ፍቃድ ባላቸው ተቋማት በኩል ግለሰቦቹን ለመያዝ ካስፈለገ ለጥቆማ እንዲያግዝ ፎቷቸውን ይፋ ያስደርጋል እንጂ ራሱ ማድረግ አይችልም፣

- ባንክ ግለሰቦችን ወንጀለኛ ማለት አይችልም፣ ፖሊስም አይችልም። ብቸኛው ይህ መብት ያለው ፍርድ ቤት እና ፍርድ ቤት ብቻ ነው 

ትናንት ይህን ድርጊት በተመለከተ አንድ መረጃ አጋርቼ "ለሌባ ጠበቃ ቆምክ፣ አንተም ወስደሀል መሰለኝ..." አይነት ዝባዝንኬ አስተያየት የሰጡ ነበሩ።

ዛሬ ይህ ተቋም ከህግ ውጪ ፎቶ ሲለጥፍ "ለምን?" ካላልን ነገ የፈለገው ድርጅት እና ግለሰብ እየመጣ ፎቶህን ለጥፎ ያሻውን ያደርጋል።

ባለኝ መረጃ መሰረት በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ላይ ያልተሳተፉ ሰዎች ጭምር ፎቷቸው ወጥቶ ፍርድ ቤት እያመሩ ነው፣ ሌሎቹ ደግሞ የወሰዱትን ብር መልሰው ፎቷቸው ግን ወጥቷል።

ሌብነትን እናውግዝ፣ ለህግ የበላይነት እና መከበርም እንቁም።

መልካም አዳር።

@EliasMeseret