Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.84K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 41

2023-02-20 21:35:41
#UPDATE በ3.8 ቢሊየን ብር ወጪ ግዢ ስለተፈፀመባቸው 200 ባሶች እና አነጋጋሪ ዋጋቸው ከአራት ቀን በፊት አንድ መረጃ አጋርቼ ነበር፣ በዚህ ዙርያ ማብራርያ ሊሰጥ እንደሚገባም ሀሳብ ሰንዝሬ ነበር።

ለማስታወስ ያህል: ከላይ በተጠቀሰው ስሌት መሰረት አንዱ አውቶቡስ የተገዛው 19 ሚልዮን ብር (ወይም 354,000 ዶላር ገደማ) እንደሆነ፣ ነገር ግን እኔ በግሌ ሁለት የቻይና መኪና አቅራቢ ድርጅቶችን አናግሬ ዋጋቸው ከ111,000- 130,000 ዶላር ገደማ እንደሆነ እንዳሳወቁኝ ፅፌ ነበር።

በዚህ ዙርያ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ጉዳዩን ያስረዳሉ ያሏቸውን ነጥቦች በስፋት አብራርተውልኛል። አቶ ምትኩ ያነሱልኝን ነጥቦች ሳልጨምር፣ ሳልቀንስ አቅርቤው አንባቢ የራሱን ግንዛቤ ይውሰድ:

- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በኩል የ200 ባስ ግዥ ተፈፅሟል። የ200 ባስ ግዥ ጨረታ ሰነዱ የቀረበው የተለያዩ ወጭዎችን ሸፍኖ ማለትም የዉጭ መንዛሬም ሆነ ለሎች ነገሮችን አጠቃሎ በአድራሻችን ማቅረብ ነበር።

- ለዚህ ግዢ ያደታ ጁነይዲ (የ Higer Bus አቅራቢው) በአነስተኛ ዋጋ አሸንፏል፣ ዋጋውም ወደ 18.9 ሚልዮን ብር ገደማ ነበር። ሁለተኛ የሆነው ድርጅት ያቀረበው 22 ሚልዮን ብር ገደማ ነበር። ይህ ግዢ በአመት ለድጋፍ ሰጪ ባሶች ከከተማ አስተዳደሩ የሚከፈለውን 600 ሚልዮን ብር አስቀርቶ ወደፊት ሌሎች ባሶችን ለመግዛት ታሳቢ ያረገ ነበር።

ዋጋው ከአውቶብሱ የታች መሸጫ ዋጋ (base price) ለምን እጅግ ከፍ ያለ ሆነ የሚለውን ጥያቄዬን ሲያብራሩ:

1ኛ: የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላለ አውቶብሶቹ የተገዙት በውጭ ምንዛሬ ሳይሆን በብር ነበር (አቅራቢው ድርጅት ዶላር በራሱ አቅርቦ)። ያናገርናቸው አንዳንድ የቻይና ኩባንያዎች ጭራሽ በዶላር እንጂ በብር ግብይት አንፈፅም ብለዋል።

2ኛ: አውቶብሶቹ የተገዙት በቀጥታ ከፋብሪካው/አምራቹ ሳይሆን ከመኪና አቅራቢ ድርጅት፣ ይህም መሀል ላይ ያለ የድርጅት ትርፍን ታሳቢ ያደረገ ነበር።

3ኛ: አውቶብሶቹ በተለያየ ማዘመኛ ስፔክ (specifications) የተገጠመላቸው ናቸው። ከቻሲስ ስር ያሉ ዋና ዋና ክፍሎቹ ከጀርመን በመጡ ምርቶች እንዲደረጉ አስደርገናል፣ ይህም ዋጋው ላይ ጭማሬ አስከትሏል።

4ኛ: እንደ ሱር ታክስ፣ ዊዝሆልዲንግ እና ቫት ያሉ ቀረጦች ተጨምረውበታል፣ ይህም ወደ 30 ፐርሰን ይደርሳል። ግዢው በዚህ መልኩ ቢፈፀምም ወደፊት እኛ ከገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን መልሰን እንጠይቃለን (ወደኋላ ተመላሽ ይሆናል)።

5ኛ: ከዛም የማስጫኛ፣ የወደብ ክፍያ፣ ኢንሹራንስ፣ ዲመሬጅ... ወዘተ ክፍያዎች ነበሩበት።
-------------------------------------------------------------

*እንደ ማንኛውም የሚድያ ስራ ሁሉንም ባላንስ ማረግ እና እኩል ቦታ መስጠት ተገቢነት እንዳለው አምናለሁ። በመግቢያው እንዳልኩት አንባቢዎች የራሳቸውን ንፅፅር አድርገው ግንዛቤ ይውሰዱ፣ በዚህ ገለፃ ለእኔ አንዳንድ መልሶችን ባገኝም አሁንም ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች እንዳሉ አሉ። ጉዳዩን ለኔ ለማስረዳት ርቀት ለሄዱት የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ግን ምስጋና

መልካም ምሽት!

@EliasMeseret
24.8K views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 21:35:28
22.5K views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 20:50:20
የፍርድ ቤት የብርበራ ማዘዣ አሳዩን ብለው የጠየቁ የሚዲያ ሠራተኞች 8 ቀን በእስር ላይ ሆነው እንዲመረመሩ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ተከራይቶ የሚሰራበት ስቱዲዮ ፀሃፊ ወ/ሮ መሰረት ታምሩ እና የካሜራ ባለሙያ አቶ አማኑኤል አስፋው በባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ለእስር መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው።

ወ/ሮ መሰረት ታምሩ እና አቶ አማኑኤል አስፋው የቪዲዮ ቀረጻ አገልግሎት ከሚሰጡበት ድርጅት የፍርድ ቤት የብርበራ ማዘዣ ፍቃድ የሌላቸው የመንግስት የጸጥታ ኅይሎች ፍ/ቤት በዋስ እንዲወጣ የፈቀደለትን ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋ ለፍተሻ እና ብርበራ በሚል ምክንያት ተከራይቶ የሚሰራበት ስቱዲዮ በማስገደድ ብርበራ አካሂደዋል ።

በድርጅቱ የሥራ ቦታ የነበሩ ሠራተኞች ፤ ፖሊስ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብርበራ አካሂዳለው ማለቱ አግባብ እንዳልሆነ እና የፍርድ  ቤት ማዘዣ ሊደርሳቸው እንደሚገባ ለጸጥታ ኃይሎች ቢገልጹም በማስገደድ ብርበራ በማካሄድ ወ/ሮ መሠረት ታምሩ እንዲሁም አቶ አማኑኤል አስፋው ከላይ በተገለፁት የፀጥታ ሀይሎች ታፍነው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተወስደው ታስረዋል።

በዛሬው ዕለት በፌደራል የመ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት፤ ከሰዓት በኋላ በዋለው ችሎት ወ/ሮ መሠረት ታምሩ እና አቶ አማኑኤል አስፋው ፤ ከጠበቆቻቸው ጋር ቀርበዋል።

ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ከፍቶ ለፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ፤ " ተጠርጣሪዎች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት በመጠቀም ፤ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት በመፍጠር ብሔርን ከብሔር በማጋጨት ፣ ሕዝብና መንግስትን ለማጋጨት ፣ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ በተደረገ ክትትል በቁጥር ሥር ውለዋል። በሰውና በሰነድ ማስረጃ ማጣራት እንድንችል ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ማጣራያ የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልን " በማለት ፖሊስ ለፍ/ቤት ጥያቄውን አቅርቧል ።

የታሳሪዎች ጠበቆች በፖሊስ በኩል ለቀረበው አቤቱታ በሰጡት ምላሽ " ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበት ጉዳይ የዋስትና መብትን የሚያስከልክል አይደለም ።

እንዲሁም ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ሕጋዊ አሰራር እንዲከተል በመጠየቃቸው እንደ አንድ ንቁ ዜጋ የሚያስቆጠር እንጂ ፤ የወንጀል ፍሬ ነገር የሌለው ከመሆኑ ባሻገር በያዛቸው አካል የሚያስመሰግን ድርጊት ከመሆኑ ባለፈ የሚያሳስራቸው አይደለም ።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ተጠርጣሪዎች የተያዙት ለምርመራው አጋዥ በሆነ መንገድ ሳይሆን ፤ በሥራ ቦታቸው ላይ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ባሉበት ጊዜ ፖሊስ ለብርበራ መምጣቱን ሲገልጽ የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ከያዙ ብርበራ ማድረግ እንደሚችሉ ስለ ተገለጸላቸው ብቻ ይህንን እንደ ሕገወጥ ተግባር በማየት ደንበኞቻችን አስሮ የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ ሕገመንግስታዊም ፣ ሥነ ሥርዓታዊም ባለመሆኑ ደንበኞቻችችን በዋስ መውጣት አለባቸው " በማለት ጠበቆች ለፍ/ቤቱ  ጠይቀዋል ።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ለፖሊስ ተጨማሪ 8 ቀን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ፤ ለየካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በይድነቃቸው ከበደ

@EliasMeseret
23.4K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 20:50:08
22.6K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 13:22:12
#ለግልፅነት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቤታቸው ስለተቃጠለባቸው የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ታህሳስ ወር ላይ አንድ የድጋፍ ጥሪ አጋርቼ ነበር። በርካታ ሰዎች ባደረጉት ትብብር አሁን ላይ የተሰበሰበው ገንዘብ 800,000 ብር ደርሷል፣ ተወካዮቻቸው ለ3 በከፈቱት የባንክ አካውንት ውስጥ ገቢ ሆኗል።

ወደ አካባቢው ለመሄድ መንገድ እንኳን አልነበረውም፣ አሁን የወረዳው አስተዳደር ወደ ከተማው አቅራቢያ የቤት መስሪያ መሬት ሰጥቷቸዋል፣ አዲስ መንደር ይገነባል።

በድጋፍ ለተሳተፋችሁ፣ መረጃውን ላጋራችሁ እንዲሁም ጉዳዩን በመጀመርያ ቀርፆ ለተመልካች ላደረሰው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ፎቶ: በፍቃድ የቀረበ

@EliasMeseret
24.6K viewsedited  10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 07:37:55
ህፃን ልጅ እንዲህ የሚደበድብ ሰው...

ስገምት ህፃኗ ልጇ ላትሆን ትችላለች፣ ብትሆንም ህፃኗን ሳትገድላት የሚመለከታቸው አካላት ጣልቃ ሊገቡ እና ሊያድኗት ይገባል። ሴትየዋን የምታውቁ ሰዎች በመጠቆም ተባበሩ።

*Update: እዚህ ቪድዮ ላይ ህፃን ስትደበድብ የምትታየው ግለሰብ ሐሊማት መሀመድ እንደምትባል፣ የዛሬ 11 ዓመት ገደማ በወንጀሉ ዙርያ ፍርድ ቤት ቀርባ 300 ብር ብቻ ቅጣት እንደተጣለባት የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

https://fb.watch/iOIdomCAs4/

@EliasMeseret
25.4K viewsedited  04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 15:37:24
ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የአፍሪካ መሪዎች ይዘው የመጡ ቅንጡ አውሮፕላኖች (private jets) በቦሌ አየር ማረፊያ።

እንዲህ ተንፈላሰው ተጉዘው መጥተውም ለአፍሪካውያን መላ ቢፈጥሩ መልካም ነበር።

Video: Aggrry Mutambo/Mahmoud Abdi

@EliasMeseret
26.5K viewsedited  12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ