Get Mystery Box with random crypto!

#Update የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙርያ ባቀረብኩት መረጃ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

#Update የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙርያ ባቀረብኩት መረጃ ላይ ያደረሰኝ መረጃ

በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ ከሚገኝ የምግብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ለተራቡ ዜጎች ተብለው የሚወጡትን የምግብ አይነቶች እዛው የንግድ ቀጠና ውስጥ ፓኬጁ ላይ ባንዲራ በመጨመር እየታሸጉ እንደሆነ አንድ መረጃ አቅርቤ ነበር።

በዚህ ዙርያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ይህን መረጃ አድርሶኛል:

"WFP procured 50,000 MT of wheat on behalf of the EDRMC from WFP’s Global Commodity Management Facility (GCMF) - WFP's regional storage facility for purchased commodities - for EDRMC’s humanitarian support to communities affected by drought, floods, and conflict in Ethiopia. The wheat purchased from WFP by EDRMC is being collected from WFP’s warehouses in Dire Dawa after it has been transferred from UN bags to those provided by the government, ready for distribution. WFP occasionally leverages its extensive procurement expertise and networks to provide food procurement services to partners allowing them to respond to food needs in a timely manner."

ለመረጃው የአለም ምግብ ፕሮግራምን እያመሰገንኩ በለጋሽ ድርጅቶች የሚገዙ የምግብ አይነቶችን 'በኢትዮጵያ የተመረተ' በሚል ማሸግያ ቀይሮ ማውጣት ለምን እንዳስፈለገ የሚመለከተው የመንግስት አካል አስተያየት ቢሰጥበት መልካም ነው እላለሁ። በቅርብ ወራት የእርዳታ ምግብ ምን ሲደረግ እንደነበር የሰማን/የምናውቅ እና እርዳታው ለተጠቃሚው ህዝብ እንዲደርስ የምንፈልግ ሁሉ ይህን መጠየቅ አለብን።

@EliasMeseret