Get Mystery Box with random crypto!

#ለግልፅነት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቤታቸው ስለተቃጠለባቸው የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ታህሳስ ወር ላይ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

#ለግልፅነት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቤታቸው ስለተቃጠለባቸው የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች ታህሳስ ወር ላይ አንድ የድጋፍ ጥሪ አጋርቼ ነበር። በርካታ ሰዎች ባደረጉት ትብብር አሁን ላይ የተሰበሰበው ገንዘብ 800,000 ብር ደርሷል፣ ተወካዮቻቸው ለ3 በከፈቱት የባንክ አካውንት ውስጥ ገቢ ሆኗል።

ወደ አካባቢው ለመሄድ መንገድ እንኳን አልነበረውም፣ አሁን የወረዳው አስተዳደር ወደ ከተማው አቅራቢያ የቤት መስሪያ መሬት ሰጥቷቸዋል፣ አዲስ መንደር ይገነባል።

በድጋፍ ለተሳተፋችሁ፣ መረጃውን ላጋራችሁ እንዲሁም ጉዳዩን በመጀመርያ ቀርፆ ለተመልካች ላደረሰው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ፎቶ: በፍቃድ የቀረበ

@EliasMeseret