Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2023-04-27 16:37:56
20.0K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 11:00:46
በፖለቲካ ውስጥ ቋሚ ጠላትነት የለም ይባላል።

እንኳንም ለዚህ አበቃችሁ፣ ሰላም ሲፈጠር የሚጠላ መቼም የሆነ ችግር ያለበት ነው። ግን ደግሞ በለኮሳችሁት ጦርነት ተለብልቦ ቁስሉ ላልዳነለት ህዝብ ስትሉ ቢያንስ ለትንሽ ግዜ intimate የሆኑ ምስሎችን እና "እንቁልልጭ" አይነት ግንኙነቶችን ብታስቀሩ ጥሩ ይመስለኛል። ለማንም ሳይሆን አባት፣ ወንድሙን፣ እህት፣ እናቱን፣ ሚስት፣ ባል ተነጥቆ፣ በሩን ዘግቶ ሲያለቅስ ለሚኖር በመቶ ሺዎች ለሚቆጠር ምስኪኑ ህዝብ ብላችሁ።

@EliasMeseret
24.0K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 15:54:37
#አይቻልም...! 

ብዙ ግዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ በሀገራችን ያለው የክልከላ እና እግድ ብዛት (መአት) ነው።

ሰልፍ ለማድረግ ሲታሰብ "ፍቃድ አልተሰጠም" ከሚለው የዘወትር አካሄድ እስከ ዶላር መያዝ የሚከለክለው ደንብ፣ ኮሽ ባለ ቁጥር ከሚዘጋው ስልክ እና ኢንተርኔት እስከ ዜጎችን እንቅስቃሴ ማገድ ተጠቃሽ ናቸው።

ለዚህ አንዱ መነሻ የሚመስለኝ ከገዥዎች ለዜጎች ያለ አተያይ ነው... የ "ምንም አያመጡም" አይነት አካሄድ። ሌላው ቀርቶ "ነዳጅ በዚህ መልኩ ትቀዳለህ" እና "ቤትህ ህገ ወጥ ስለሆነ ይፈርሳል"ተብሎ የሚኬድበት ሂደት በራሱ ይመሰክራል፣ የህዝብ አስተያየት እና ምክክር ሳይጠየቅ ተግባራዊ ይደረጋል።

በሌላ ሀገር መንግስት የስልጣኑ ምንጭ የሆነውን ህዝብን ይፈራል፣ እኛ ሀገር ህዝብ (እንዲሁም በሚደንቅ መልኩ የህግ አውጪ የህዝብ እንደራሴዎች ጭምር) መንግስትን ይፈራሉ፣ ብናገር ምን ይመጣብኝ ብለው ይሰጋሉ።

"Politics brings out the worst in people" የሚለውን አባባል በሚያጠናክር መልኩ "ለምን?" ብሎ ለህዝብ የሚቆመው ፖለቲከኛ ጥቂት ነው። ወይ ለራሱ ይሰጋል፣ ወይ የክልከላው እና እግዱ አባሪ እና አስተባባሪ ነው።

ግን ግፍ ተጠራቅሞ እና ህዝብ መሮት በቃኝ ያለ ቀን...

@EliasMeseret
15.9K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 13:19:58
#ሰላም በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚለው) መሀል ዛሬ በታንዛንያ የሚጀመረው ንግግር ቢያንስ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት፣ ከፍ ካለም በቀጣይ ሳምንታት በሚቀጥሉ ውይይቶች እና ንግግሮች ወደ ሰላም ስምምነት እንደሚሸጋገር ያላቸውን ተስፋ እና ግምት በጉዳዩ ዙርያ ያነጋገርኳቸው ዲፕሎማቶች እና የቀጠናው ተንታኞች ጠቁመዋል።

ይህ ውይይት በይፋ ከመነገሩ በፊት በርካታ ተመሳሳይ ሙከራዎች በተለይ በናይሮቢ ሲደረጉ ነበር። ይሁን እንጂ በተለያየ ወቅት በሁለቱም አካላት በውይይቶቹ ላይ አለመገኘት፣ አጀንዳ መቀየር እና የተወያዮች ጉዞ መስተጓጎል ሊያሳካው አልቻለም ነበር (በዚህ ዙርያ ብዙ ዝርዝሮች ቢኖሩኝም ለግዜው ይቅር)።

ምናልባትም የዛሬው ቀን በኦሮሚያ ክልል ለሚኖረው ህዝባችን የሰላም ጭላንጭል የሚፈነጥቅበት ይሆናል ብለን ተስፋ እናድርግ።

ዜጎች በጅምላ ሲጨፈጨፉ፣ ታጣቂ ቡድኑን ትደግፋላችሁ ተብለው የአካባቢው ወጣቶች ሲታሰሩ እና ሲገደሉ፣ የታጣቂዎች ማሰልጠኛ አጠቃን ተብሎ የአካባቢው ህዝብ በድሮን ሲመታ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው... የተወሰኑትን ለማቅረብ ስሞክር ነበር።

ውጤቱን ያማረ ያድርገው።

በወቅቱ "ለሸኔ ስልታዊ ድጋፍ ማድረግህ ነው?" የሚል መልእክት ከአንድ ቱባ ካድሬ እንዲደርሰኝ ምክንያት የሆነ ይህ ደብዳቤ ልክ የዛሬ አራት ወር ለጠ/ሚር አብይ አህመድ በኦሮሚያ ያለው ግጭት በሰላም እንዲፈታ የፃፍኩት እና በዚህ ማህበራዊ ሚድያ ያጋራሁት ደብዳቤ ነበር።

@EliasMeseret
17.1K views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 12:41:00 ሰላም!

ከሁለት ወር (February 25- April 25) ቆይታ/እረፍት በኋላ አንዳንድ መረጃዎች አሁን መቅረብ ይጀምራሉ።

መልካም ቀን!

@EliasMeseret
17.6K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 05:06:33
#ተነስቷል ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

መልካም በዓል!

@EliasMeseret
8.9K views02:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 23:20:05
#እውነታው ኢቢሲ ከትናንት ጀምሮ "ኦፕን ማጋዚን የሚባል የህንድ መፅሄት በአፍሪካ የዲሞክራሲያዊ መሪዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ፣ ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድን በ1ኛ ደረጃ ላይ አስቀመጠ" የሚል ዘገባ ይዞ ሲወዘውዘው ነበር።

የእሱን መረጃ ይዘው ደግሞ የሀገሬ የሶሻል ሚድያ ገፆች እና የዩትዩብ ቻናሎች ሲቀባበሉት ነበር። ከኢቢሲ በተጨማሪ አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ፣ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኦቢኤን አማርኛ... ወዘተ መረጃውን ሲያጋሩ ነበር።

የመፅሄቱ ዋና ኤዲተር ኤስ ፕራሳናራጃን በዚህ ዙርያ መረጃ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን ያደረሰ ሲሆን "እኛ እንዲህ አይነት መረጃ አላወጣንም፣ የእኛም ዘገባ አይደለም። ይህንን ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን" የሚል ምላሽ ልኳል።

በዲጂታል መልኩ የታተሙ የመፅሄቱን የቅርብ ግዜ ህትመቶች የተመለከትኩ ሲሆን የተጠቀሰው አይነት መረጃ ይዘው እንዳልወጡ ማየት ይቻላል።

ከሁሉም የሚገርመው ግን የዚህ ሀሰተኛ መረጃ መነሻ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ ስም ተመሳስሎ በተከፈተ አንድ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ይቻላል። ይህ አካውንት ደግሞ ሀሰተኛ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ በተከታታይ መረጃዎችን አቅርቦ ነበር።

ይቺን እንኳን ሳያጣሩ ለሚልዮን ተከታታዮች መረጃ ማቅረብ አይከብድም... ወይም እንደ ክበበው ገዳ አባባል "አይሰቀጥጥም"?

*በኢንቦክስ ጥያቄ ሲበዛ ጎራ አልኩ፣ አሁን ወደ social media break/detox

መልካም አዳር፣ በሌላ ፌክ ኒውስ በቅርቡ እንገናኝ

@EliasMeseret
36.6K viewsedited  20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 14:03:00 የ "U.S.A" ጎረቤት የሆነ ሀገር ጥራ ሲባል "U.S.B" እንዳለው ልጅ ሁሉ ቦረና ረሀብ ገባ ሲባል ሸራተን ድግስ

#አዬ በዚሁ ትንሽ ዞር ልበል፣ ቸር ሰንብቱ

@EliasMeseret
30.7K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 13:34:43
#UPDATE በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ውስጥ ስለተከሰተው እጅግ አሳሳቢ ድርቅ እና ረሀብ ዙርያ እስካሁን ከአካባቢው አርብቶ አደሮች፣ የስራ ሀላፊዎች እና የጤና ባለሙያዎች በግሌ ለማሰባሰብ የቻልኩት መረጃ:

- እንደ ተልተሌ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ ለቁጥር አንድ፣ ሁለት እንኳን የሚባል የተረፈ ከብት የለም። እስካሁን 3.2 ሚልዮን ከብቶች አልቀዋል፣ በአካባቢው ያለው የሞተ ከብት ሽታ እጅግ ይረብሻል።

- በአንዳንድ ሀላፊዎች ሚድያዎች ላይ ማስተባበያ ቢደረግም ተልተሌ ወረዳ ላይ ቢያንስ ሰባት ሰዎች በምግብ እጥረት እና ተያያዥ መንስኤዎች ህይወታቸው አልፏል፣ በርካታ ተጨማሪ ሰዎች እንዳይሞቱ ከፍተኛ ስጋት አለ።

- አንዳንዶች ተስፋ በመቁረጥ ድንበር ተሻግረው ወደ ኬንያ እየሄዱ ይገኛሉ፣ በኬንያ በኩልም ድርቅ ስላለ ያሉበት ሁኔታ አስጊ ነው።

- ይህ ከፍተኛ አደጋ የተከሰተው ለተከታታይ 5ኛ አመት ዝናብ ባለመዝነቡ ነው፣ በዚህ ሁሉ ግዜ ግን እንደ ውሀ እና የከብት እህል ያሉት ላይ በቂ ዝግጅቶች ስላልተደረጉ የሆነው ነገር ተከስቷል።

- አሁን ላይ 600,000 ሰው ከብቱ አልቆበት በመጠለያ ገብቶ ህይወቱን ለማትረፍ እየሞከረ ነው። ነገር ግን ለእነዚህ ዜጎች ከፌደራልም ሆነ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እየቀረበ ያለው ድጋፍ የፍላጎቱ 2 ፐርሰንት ብቻ ነው።

Photo: Jan. 2022 UNICEF

@EliasMeseret
30.7K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:03:33
የአድዋ ድል ሲዘከር የአጤ ምኒሊክ ምስል ለፖስተር እንኳን አይበቃም?

#ታሪክንበጠረባ

@EliasMeseret
28.6K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ