Get Mystery Box with random crypto!

#አይቻልም...!  ብዙ ግዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ በሀገራችን ያለው የክልከላ እና እግድ ብዛ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

#አይቻልም...! 

ብዙ ግዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ በሀገራችን ያለው የክልከላ እና እግድ ብዛት (መአት) ነው።

ሰልፍ ለማድረግ ሲታሰብ "ፍቃድ አልተሰጠም" ከሚለው የዘወትር አካሄድ እስከ ዶላር መያዝ የሚከለክለው ደንብ፣ ኮሽ ባለ ቁጥር ከሚዘጋው ስልክ እና ኢንተርኔት እስከ ዜጎችን እንቅስቃሴ ማገድ ተጠቃሽ ናቸው።

ለዚህ አንዱ መነሻ የሚመስለኝ ከገዥዎች ለዜጎች ያለ አተያይ ነው... የ "ምንም አያመጡም" አይነት አካሄድ። ሌላው ቀርቶ "ነዳጅ በዚህ መልኩ ትቀዳለህ" እና "ቤትህ ህገ ወጥ ስለሆነ ይፈርሳል"ተብሎ የሚኬድበት ሂደት በራሱ ይመሰክራል፣ የህዝብ አስተያየት እና ምክክር ሳይጠየቅ ተግባራዊ ይደረጋል።

በሌላ ሀገር መንግስት የስልጣኑ ምንጭ የሆነውን ህዝብን ይፈራል፣ እኛ ሀገር ህዝብ (እንዲሁም በሚደንቅ መልኩ የህግ አውጪ የህዝብ እንደራሴዎች ጭምር) መንግስትን ይፈራሉ፣ ብናገር ምን ይመጣብኝ ብለው ይሰጋሉ።

"Politics brings out the worst in people" የሚለውን አባባል በሚያጠናክር መልኩ "ለምን?" ብሎ ለህዝብ የሚቆመው ፖለቲከኛ ጥቂት ነው። ወይ ለራሱ ይሰጋል፣ ወይ የክልከላው እና እግዱ አባሪ እና አስተባባሪ ነው።

ግን ግፍ ተጠራቅሞ እና ህዝብ መሮት በቃኝ ያለ ቀን...

@EliasMeseret