Get Mystery Box with random crypto!

#የሚድያነፃነት የዛሬ 5 አመት ግንቦት 2011 ዓ/ም ላይ የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ኢትዮጵያ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

#የሚድያነፃነት የዛሬ 5 አመት ግንቦት 2011 ዓ/ም ላይ የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ አዘጋጅታ ነበር፣ በፕሮግራሙ ላይ ከዓለም ዙርያ የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ታድመው ነበር፣ እኔም ተገኝቼ ነበር።

እለቱ በኢትዮጵያ እንዲከበር የተደረገው በወቅቱ በእጅጉ ተሻሽሎ የነበረውን የፕሬስ ነፃነት recognition ለመስጠት ጭምር ነበር። የተደረጉት ንግግሮች፣ ቃል የተገባባቸው ጉዳዮች እና ተስፋ ሰጪ ምልክቶች በርካቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ስርዐት ውስጥ ለበርካታ አመታት በችግር ውስጥ ጋዜጠኝነት እንደሰራ አንድ ባለሙያ እኔም ተስፋ ታይቶኝ ነበር። 

ዛሬስ?

ዛሬ ላይ ያ ሁሉ ተቀይሮ ከድሮው እጅግ የባሰ የፕሬስ መብት ረገጣ ያለበት ግዜ ሆኗል። ጋዜጠኛ አይደለም ስህተት ሰርቶ ገና ለገና ለተቃዋሚ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል፣ ግፎችን ሊያጋልጥ ይችላል እና ሚስጥር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ ወደ እስር ቤት ተግዟል።

ከሰሞኑ እየሰማሁት እንደሆነው ደግሞ የመንግስት ሚድያዎች ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ጭምር ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እየገቡ ነው። በባለስልጣናት ቀጭን ትእዛዝ ይህን ዘግብ፣ ያንን አትዘግብ እየተባሉ ማስፈራርያ ጭምር እየደረሰባቸው ነው። ሌላው ቀርቶ አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሙስናና እና ሌሎች ወንጀሎች ሰራተኞቻቸው ሲታሰሩ "የቀድሞ ሰራተኛ ብላችሁ ዘግቡ" በማለት በተለይ የመንግስት ሚድያዎችን እያስገደዱ ይገኛሉ።

"በፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ለምን ዜና አልሰራህም?" ተብሎ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከስራው የተባረረው ነፍሱን ይማረው ጋዜጠኛ በቀለ ሙለታ አንድ ምስክር ነበር። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን፣ ከኢዜአ፣ ከኢቲቪ፣ ከፋና... ወዘተ ስራቸውን የለቀቁም አሉ።

Free the media!

@EliasMeseret