Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-03-08 15:26:13
ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ልታገኝ ባሰበችው የባህር በር ምትክ ለሱማሊላንድ ልትሰጥ ያሰበችውን የሀገር እውቅና ለመተው እያሰበች እንደሆነ አለም አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡ ነው።

እኔም ከሰሞኑ በተካፈልኩበት አንድ የዲፕሎማቲክ አባላት መግለጫ ላይ ይህ ጉዳይ የተነሳ ሲሆን "አንድም ከአለም አቀፍ አጋሮች፣ ሀገራት እና ተቋሟት በተሰነዘረ አስተያየት እና በተደረገ ጫና...ሁለትም አሁናዊ አለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ክስተቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሱማሌላንድ እውቅና መስጠት የሚለው ሀሳብ እንደማያስኬድ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግንዛቤ እንደተወሰደ እናውቃለን" የሚል አስተያየት ተሰጥቷል።

በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የመግባብያ ስምምነቱ ተግባራዊ ቢሆን የሁቲ አማፅያንን ጨምሮ በአካባቢው ያሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ መፍትሄ እንደሆነ ተደጋግሞ የተነሳ እንደነበር፣ ይህም ከዩናይትድ ኪንግደም አቋም ጋር ቢመሳሰልም ዩኬ ሀሳቧን ወደ መሬት ለማስረገጥ እንዳልቻለች ይጠቅሳሉ።

በሱማሌላንድ በኩል በዚህ ዙርያ እስካሁን አስተያየት ያልተሰጠ ሲሆን ከዚህ ቀደም ግን 'እውቅና ከሌለ ስምምነቱም የለም' (No recognition, no deal!) ብለው ደጋግመው ተደምጠው ነበር።

Image via Bloomberg

@EliasMeseret
26.2K viewsElias M, 12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 14:45:40 ትክክለኛው የአገር ፍቅር መገለጫ እና ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም ማስከበሪያ አስተሳሰብ የቱ ነው?

የአገር ፍቅር/የአገር ተቆርቋሪነት እና ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም መሬት ላይ ያለውን እውነታ በመካድ "ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ" በማለት ብቻ ሊረጋገጥ አይችልም። ከንቱ መፈክሮች ብቻቸውን በደመነፍስ ከሚደግፍና ከሚቃወመው Hooligan ጭብጨባ እና ሆይሆይታ ከማስገኘት ባለፈ የአገርን ጥቅም በተጨባጭ ሊያስከብሩ አይችልም።

እውነታውን ለመጋፈጥ ባለመዘጋጀት እና የችግሮችን ምንጭ በቅጡ መርምሮ ባለመረዳትና ችግር የወለዳቸውን ሁነቶችን ብቻ በመኮነንና ሰዎችንም በማጥላላትና በመፈረጅ  የሚጠበቅ አገርም ሆነ አገራዊ ጥቅም የለም፣ የሚፈታ ችግርም አይኖርም።

ያረጀ ያፈጀ ጀብደኝነት እና ጠርዝ-ረገጥ አገራዊም ሆነ ማህበረሰባዊ ብሄርተኝነት ያገር ፍቅር ወይም የማህበረሰባዊ ወገንተኝነት መገለጫ አይሆኑም። ፖለቲከኞች አንዴ የአጉል አገራዊ ብሄርተኝነት ስሜቶችን በሌላ ጊዜ ደግሞ ጠርዝ-ረገጥ የማህበረሰባዊ ማንነት ስሜቶችን በመኮርኮር የፖለቲካ አላማቸውን ለማሳካት የሚጠቀሙበት ሆሊጋን መሆንም አይገባም።

የአገር ፍቅር የሚገለፀውና ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም የሚከበረው ከእውነታው ጋር በመታረቅ እና ተጨባጭ ካልሆነ ምዕናባዊ አገር ወደ እውነተኛዋ ኢትዮጵያ ስንመለስ ነው።

የማህበረስቡን ችግር የማስተባበያ ሰበብ ከመፍለግና ችግሩ በሃሳባቸው የማትስማማባቸው ሰዎች ስላነሱት ብቻ ችግሩን አቃሎና አራክሶ ከማየት ይልቅ ችግሩን በነፃ አዕምሮ በተጎጂዎች ጫማ ውስጥ ሆኖ ለመረዳት በመሞከርና በእነሱ ቦታ ብሆን ምን አይነት የተስፋና የመፍትሄ ሃሳብ ላመነጭ እችል ነበር ብሎ ማሰብ ሲቻል የአገር ጥቅም ይከበራል።

ወደ ተጨባጩ አለም ስንመጣ የአገራችንን ሁኔታ በውል የሚወስኑ ጉዳዮችን በአግባቡ ለመለየት አዕምሯችን ክፍት ይሆናል። በደፈናው የምንፈርጃቸውን ሰዎች ትክክለኛ የተግባራው እምጃ መነሻ ምክንያቶችንም ሆነ የራሳችንን ክፍተት ለመለየት እንላለን። መሬት የያዘ pragmatic የመፍትሄ አማራጮችንም ማምጣት ይቻላል።

Via Tilahun Adamu

@EliasMeseret
24.8K viewsElias M, edited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 14:10:21 #Update የካቲት 11/2016 ዓ/ም ምሽት ላይ በቦሌ አየር ማረፊያ በአንድ ተጓዥ ላይ ስለተፈፀመ ድርጊት በቅርቡ መረጃ አቅርቤ ነበር

በዕለቱ በስፍራው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት መቅረባቸውም ታውቋል።

በወቅቱ ያቀረብኩት መረጃ ይህ ነበር

ስሟን የማልጠቅሳት ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ተጓዥ ማታ 5 ሰአት ወደ አሜሪካ ላለባት ጉዞ ቀደም ብላ 2 ሰአት ቦሌ ኤርፖርት ትደርሳለች።

በፍተሻው ወቅት "ሻንጣሽን ከፍተሽ አሳዪን፣ ማሽኑ የሆነ ነገር ያሳየናል" በማለት ሻንጣዎቿን አስከፈቱ። በዚህ ወቅት የያዘችውን የግል መገልገያ ጌጣጌጥ እና በህጋዊ መንገድ የያዘችውን ዶላር ይመለከታሉ። ቀጥላም ሁኔታውም ስታስረዳኝ እንዲህ ብላለች:

"እነዚህ ለብዙ አመታት ያደርግኳቸው ከቤተሰቦቼ እንዲሁም ከባለቤቴ የተሰጡኝ ጌጣጌጦች ናቸው። የሌላ ሀገር ዜግነት ላለው ዶላር እስከ 10,000 በህጋዊ መንገድ ይፈቀዳል፣ እኔ የያዝኩት ከዚህ በጣም ያነሰ ነበር። ጌጣጌጥ ደግሞ ማስመስገብ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር። ስለዚህ ፈታሿን ይቅርታ ከዚህ በሗላ አስመዘግባለሁ አልኳት፣ ከዛም በሊፍት አድርጋ ለብቻዬ የሆነ ቦታ ወሰደችኝ።"

"በዚህ ወቅት ሌሎች ሰራተኞች 'በጥሺላት' እና 'በቃ ስጫት' ይሉኝ ነበር። እኔም ግራ ገብቶኝ የእኔ መሆኑን ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ጌጣጌጡ የሚታይበት የድሮ ፎቶ ላሳያችሁ ብላቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም። ከዛም ተለቅ ወዳለች ሌላ ሴትዮ ጋር ወሰደችኝ። የሴትዮዋ መልስ ደግሞ 'የሀገሪቱን ሁኔታ አታውቂም? ሀገሪቷ እኮ ወርቅ ያስፈልጋታል!' ነበር።"

"በዚህ ሁሉ መሀል ይቺ ትልቅ ሴትዮ ተስማሚ፣ ካልሆነ በሙሉ ይወረሳል አለችኝ። ምን ማለት ነው ስላት በግልፅ ወርቁን አካፍዪ አለችኝ። በዚህ ወቅት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። እንደማይለቁኝ ስለገባኝ፣ ስልክ እንዳወራም ስለከለኩሉኝ ብዙ ትዝታዬ ያለበትን ጌጣጌጤን ከሚወስዱ ከእሱ ውጪ እንስማማ አልኳቸው።"

"ከዛም ወደ ቦርሳዬ እየጠቆመች 'እሺ ዶላር ይዘሽ አይቻለሁ፣ እሱን አምጪ አለችኝ'። የያዝኩት ዶላር እና ብር ደግሞ የራሴንም፣ የዘመድ እና ጓደኛም ብዙ ትርፍ ሻንጣ ስለያዝኩ ለእሱ የምከፍለው ነው አልኩ። ክፈችው ብላ ትንሽ አስቀርታ የምትፈልገውን ወሰደች። ተባብረንሽ ነው የለቀቅንሽ ብለው ሂጂ አሉኝ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ የመጨረሻ ተሳፋሪ ሆኜ ወደ ጉዞዬ ቀጠልኩ።"

Note 1: ከበርካታ ወራት በፊት እንዲህ አይነት ኤርፖርት ላይ በፀጥታ እና ፍተሻ አካላት በተለይ ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ዜጎች ላይ የሚፈፀም ዝርፊያን መረጃ አቅርቤ ነበር። ይህ ተጨማሪ ማሳያ ነው።

Note 2: በኤርፖርት ያሉ እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሲነሱ አንዳንዶች በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያያይዙታል፣ ነገር ግን የኤርፖርት ጥበቃ የሚከናወነው በአየር መንገዱ ሳይሆን በሌሎች የመንግት የደህንነት እና የፅጥታ አካላት ነው።

Photo: File

@EliasMeseret
24.1K viewsElias M, edited  11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 14:10:16
23.1K viewsElias M, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 01:20:55
የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሀርቫርድ የሚኒስትሮች አመራር ፕሮግራምን በዳይሬክተርነት መቀላቀላቸው ታውቋል

በኮቪድ ወቅት በሳል አመራር በመስጠት የሚታወቁት ዶ/ር ሊያ የሀርቫርድ የሚኒስትሮች አመራር ፕሮግራምን በአሜሪካን ሀገር በሀላፊነት ደረጃ መቀላቀላቸው ታውቋል።

የዛሬ 12 አመት ገደማ የተቋቋመው ይህ ፕሮግራም በጤና፣ ፋይናንስ፣ ትምህርት እና ሌሎች ዘርፎች ለአፍሪካ፣ ደቡብ-ምስራቅ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን እስካሁን ከ66 ሀገራት የተውጣጡ 262 ሚኒስትሮች ተሳትፈውበታል።

ዶ/ር ሊያ በሚኒስትርነት ወቅታቸው ከስራ ባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም እኔ በግሌ እስከማውቀው ከሚድያ ሰራተኞች ጋርም ተናበው በመስራት አርአያ የሆኑ ናቸው።

ይህን በግሌ ያጋጠመኝን ላንሳ... ኮቪድ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ የውጭ ተጓዦች በአስገዳጅ ሁኔታ ኳረንቲን በሚገቡበት ወቅት የሆነ ነው።

አንድ ምሽት (እኩለ ለሊት ገደማ) ማህበራዊ ገፆቼን የሚከታተል በግሌ ከማላወቅው ግለሰብ "አባቴ አዲስ አበባ የሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ኳረንቲን ገብቶ ይገኛል፣ የስኳር በሽተኛ ነው። ከፍተኛ ህመም እንደተሰማው ቅድም ነግሮኝ ነበር፣ መድሀኒት እንኳን የሚሰጠው የለም። ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስደውልልለት ስልኩ አይሰራም፣ ህይወቱ አልፎ ይሆን ብለን ተጨንቀናል" ብሎ መልዕክት ላከልኝ።

ሆቴሉን ጨምሮ ወደማውቃቸው ሰዎች ስደውል "ማንም ሰው ኳረንቲን መግባት አይችልም ተብለናል" የሚል ነበር።

በመጨረሻም መልዕክቱን ለዶ/ር ሊያ በለሊት ላኩላቸው። ወዲያውኑ ወደ ሆቴሉ አምቡላንስ አስልከው ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ፣ የግለሰቡ ህይወት ባይተርፍም የእርሳቸው ከፍ ያለ ትብብርን ግን አስታውሳለሁ።

መልካም የስራ ግዜ።

@EliasMeseret
14.9K viewsElias M, 22:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-07 18:32:29 #ጥቆማ ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት፣ ለንግድ ባንክ እና ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት!

ከ180,000 በላይ ተከታይ ያለው አንድ ቬሪፋይድ የሆነ የቴሌግራም ቻናል ፈጣን የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እየሰበሰበ ይገኛል።

በ15 ቀን ፖስፖርት ለማግኘት 4,500 ብር፣ በ10 ቀን 6,800፣ በ5 ቀን 8,000 ብር እና በ2 ቀን 12,000 ብር በማለት በግለሰብ ስሞች በተከፈቱ የንግድ ባንክ አካውንቶች እየሰበሰቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ብቻ በደረሱን ጥቆማዎች ገንዘብ እየተሰበሰቡባቸው ያሉት አካውንቶች "አስረስ" በተባለ ግለሰብ የአካውንት ቁጥር 1000533898908 እንዲሁም 'ህይወት' በተባለች ግለሰብ የአካውንት ቁጥር 1000522976303 ነው።

እነዚህ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኛ በመምሰል ግለሰቦችን የሚቀርቡ አጭበርባሪዎች የቴሌግራም አካውንታቸው እውነት እንዲመስል ለቴሌግራም ክፍያ በመፈፀም ቬሪፋይድ አስደርገዋል። ፖስፖርት ለማግኘት በጣም እየተንገላታ ያለውን ህዝብ ታርጌት በማድርግ እየመዘበሩ ይገኛሉ።

የእኔ ጥያቄ...

- እነዚህ ግለሰቦች መቸም የባንክ አካውንት ካለ መታወቂያ አይከፍቱም፣ ህዝብ ዘርፈው ካለተጠያቂነት መጥፋት ወይም መሰወር ይችላሉ?

- ግለሰቦቹስ የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ናቸው? (ተቋሙን ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም)

- የኢትዮጵያ የፋይናንስ አገልግሎት ደህንነት እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲህ ህጋዊ የባንክ አካውንቶችን ተጠቅመው ህዝብ በሚዘርፉ ዙርያ ምን እየሰራ ነው?

- የኢሚግሬሽን ቢሮውስ ትክክለኛ የማህበራዊ ገፆቹን ደጋግሞ በማስተዋወቅ ለምን ይህን ወንጀል አይከላከልም?

(ለማንኛውም ትክክለኛው እና በድረ-ገፁ ላይ የተቀመጠው የኢሚግሬሽን ቴሌግራም አካውንት ይህ ነው: https://t.me/ICS_Ethiopia)

Via Ethiopia Check

@EliasMeseret
22.2K viewsElias M, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-07 18:32:17
20.2K viewsElias M, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 23:42:48
#ጥንቃቄ ትናንት ከአንድ አጭበርባሪ ጋር የነበረኝ ምልልስ!

አንድ ግለሰብ 'Expats in Addis Ababa' ስለሚባል የፌስቡክ ግሩፕ ጥቆማ ላከልኝ። ጥቆማውን ተከትዬ "የውጭ ሀገር ዜጋ ነኝ፣ ስራ ጨርሼ ወደ ሀገሬ ልመለስ ስለሆነ እቃ እየሸጥኩ ነው" የሚሉ ሰዎችን ገዢ በመምሰል ማነጋገር ጀመርኩ።

እነዚህ የተገለገልንበትን እቃ እንሸጣለን የሚሉ ሰዎች አብዛኞቹ በውጭ ሀገር ሰዎች ስም የፌስቡክ አካውንት የከፈቱ ናቸው። ከዛም ይህን እቃ መግዛት እፈልጋለሁ ስትሉ ቀብድ ተቀብሎ መጥፋት።

ይህ ከላይ የምትመለከቱት ግለሰብ 'Tasha Williams' የሚል የፌስቡክ ስም ያለው ሲሆን እቃ መግዛት እፈልጋለሁ ብላችሁ ስትቀርቡ 6,000 ብር ቀብድ ይጠይቃል። ከዛ ውጭ ግን አድራሻው ለቡ ነው ከማለት ውጪ በትክክል የት እንደሆነ አይናገርም፣ ስልክ ቁጥሩን አይሰጥም፣ በስልክ ማውራትም አይፈገልግም። ቀብድ ላክልኝ ብሎ ግን 'አሸናፊ' በተባለ ግለሰብ የተከፈተ የንግድ ባንክ አካውንት ይልካል። Tasha ከሆነ ለምን አሸናፊ ብላችሁ ስትጠይቁ መልሱ: አሸናፊ ባለቤቴ ነው መልስ ነው።

ይሁን ብዬ ሁለት በሌላ የፌስቡክ አካውንት እዚሁ የፌስቡክ ግሩፕ ላይ እቃ እንሸጣለን ብለው የሚያስተዋውቁ ሰዎችን በሜሴንጀር አወራሁ፣ አሁንም ቀብድ የሚጠይቀው ይኸው አሸናፊ የተባለው ግለሰብ በዚሁ የባንክ አካውንት ነው።

በመጨረሻም ብሎክ አርጎኝ ጠፋ። ከእንዲህ አይነት አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ።

@EliasMeseret
25.7K viewsElias M, edited  20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 19:29:32
#FlightWonder ዛሬ አሁን፣ በዚህ ደቂቃ 17,000 አውሮፕላኖች በረራዎችን በአለም ዙርያ እያከናወኑ ይገኛሉ።

የዩክሬን የአየር ክልል ተለይቶ ከበራራ ነፃ እንደሆነ ያሳያል፣ ከሩስያ ጋር ባለው ግጭት አደጋ ሽሽት መስመር በመቀየራቸው።

Via Flight Radar

@EliasMeseret
29.6K viewsElias M, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-05 20:27:15
#መልካምዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁን ካሉት አውሮፕላኖች በግዝፈቱ የሚልቅ 777X የተባለ አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት ስምምነት ፈፀመ

አየር መንገዱ ስምምነቱን ዛሬ የፈፀመው እነዚህን ቢያንስ የነጠላ ዋጋቸው 440 ሚልዮን ዶላር (24.6 ቢልዮን ብር) የሆኑ ስምንት አውሮፕላኖች ለመግዛት ሲሆን ይህም የውሉን ዋጋ ከ 3.5 ቢልዮን ዶላር (197 ቢልዮን ብር) በላይ ያደርገዋል። ውሉ አየር መንገዱ እስከ 20 ተጨማሪ አውሮፕላኖች ለመግዛት መብት እንደሚሰጠው ቦይንግ ያወጣው መግለጫ ያሳያል።

የእነዚህ ቦይንግ 777X (777-9) አውሮፕላኖች ግዢ አየር መንገዱን ከአፍሪካ ቀዳሚ ያደርገዋል።

ቦይንግ 777X አውሮፕላኖች የድሪምላይነር አውሮፕላን ሞዴል መሰል ሆነው የተሰሩ ሲሆን በተሻለ መልኩ የዘመኑ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለታል። አውሮፕላኑ የተሰራበት ካርበን ፋይበር የነዳጅ ወጪውን እስከ 10 ፐርሰንት እንዲቀንስ ያደርገዋል ተብሏል።

@EliasMeseret
28.9K viewsElias M, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ