Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-03-13 19:55:34
ንግድ ባንክ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ማባረሩ ተሰምቷል

ባንኩ ከሰሞኑ ሀሰተኛ የትምህርት ሰነድ አቅርበዋል በሚል ከስራ ያባረራቸው ሰራተኞቹ ባለፈው አመት ንግድ ባንኩ ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተወዳድረው በማለፍ በስራ ላይ የነበሩ መሆናቸውን ዋዜማ ሬድዮ ዘግቧል።

ሙሉ ሪፖርቱን ለማንበብ: https://www.facebook.com/share/p/acvaaFJnjrUyoFWx/?mibextid=oFDknk

ግልባጭ: ለኢቢሲ

@EliasMeseret
23.4K viewsElias M, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-12 16:33:33
#መልካምጅማሮ በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች!

በአፈሙዝ ሰላም እንደማይመጣ፣ ይልቅ የሰው ህይወትን እንደሚያረግፍ እና ሀገር እንደሚያመሰቃቅል ምስክር እና ምሳሌ ነን።

በትግራይ ጦርነት ወቅትም ደጋግሜ ብዬዋለሁ፣ በኦሮሚያ በሚካሄደው ግጭት ዙርያም ለጠ/ሚር አብይ አህመድ 'ግልፅ ደብዳቤ' በሚል መልእክት የዛሬ አመት ገደማ አቅርቤዋለሁ፣ በአማራ ክልል ባለው ግጭት ዙርያም የዛሬ አምስት ወር ገደማ  ደግሜ ሀሳቤን አቅርቤዋለሁ።

አሁንም ልድገመው... በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የሚካሄዱ ግጭቶች በሰከነ እና የሀገርን ጥቅም ባስቀደመ መልኩ በሚካሄዱ ንግግሮች እንዲፈቱ የሚመለከታቸው አካላት ያስቡበት። ይህ ዛሬ ከመንግስት የተሰማው አቅጣጫም ይበል ያሰኛል።

ህዝቡም ይህን በመደገፍ ለሰላም ይጣር፣ ስለ ሰላም የሚያወሩ ድምፆች አይታፈኑ፣ ጦርነት ጎሳሚዎች አደብ ይገዙ ዘንድ ድምፅ አሰሙ።

Peace in our time!

@EliasMeseret
17.5K viewsElias M, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-12 15:12:36
ትክክለኛው አካሄድ ይሄ ነው!

እንደ ትራንስፖርት ሚኒስትሩ "የውጪ ሀይሎች እጅ አለበት" አይነት ችግሮችን externalize የማድረግ አካሄድ የትም እንደማያደርስ ትምህርት ሆኖ ሊያልፍ ይገባል።

#FlyEthiopian

@EliasMeseret
19.7K viewsElias M, 12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 21:44:49
እንጀራ ፍለጋ ወጥተው በቁጥጥር ስር የዋሉ 246 የደቡብ ተወላጅ ወጣቶች ጉዳይ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የህዳሴ ግድብ ግንባታ አካባቢ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ዙርያ ዛፎች መቁረጥን ጨምሮ ጫካውን የመመንጠር ስራዎችን ለመከወን በወጣው ጨረታ ኒኮትካ ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት ጨረታውን አሸንፎ ነበር።

በዚህም መሰረት ተቋማቱ ውል በመግባት የሰው ኃይል ቅጥርን በጊዜያዊነት እንዲፈፅሙ መፃፃፋቸውን ይህ ዛሬ ያገኘሁት መረጃ ያሳያል።

እነዚህ ደብዳቤዎች እንደሚያሳዩት እነዚህ ወጣቶች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሠራተኛና ማህበራዊ  ጉዳይ ቢሮ በጠየቀው መሰረት ቢሮው በተዋረድ በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳን ጨምሮ ከኧሌ እና አሪ ዞን የምንጣሮ   ስራዎችን መስራት የሚችሉ የጉልበት ሠራተኞችን መልምለዋል።

ነገር ግን ሠራተኞቹ በጉዟቸው የአማራ ክልል ሲደርሱ በታጠቁ አካላት ከመኪና ወርደው እንደተወሰዱ ከሰሞኑ ተሰምቷል።

በዩትዩብ ቻናሎች እና ሌሎች የማህበራዊ ሚድያ ገፆች እንደተባለው እነዚህ ምስኪን እንጀራ ፈላጊዎች እንጂ ተዋጊዎች/ታጣቂዎች/ወታደሮች አይደሉም።

በሰላም ተለቀው ወደየቤተሰቦቻቸው እንደሚመለሱ ተስፋ እናድርግ።

Photo: Derashe Negn

@EliasMeseret
25.0K viewsElias M, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 20:59:58
ከደብረ ማርቆስ ከሚደርሱኝ መረጃዎች!

በከተማው በመከላከያና ፋኖ መካከል በነበረው እና አሁንም እየቆየ በሚያገረሸው ጦርነት የንግድ ሱቆች ለበርካታ ወሮች ዝግ ነበሩ፣ ስራ መስራት አልቻሉም ነበር፣ በዛ ላይ አብዛኞቹ የንግድ ሱቆች በጥይት የተበሳሱና ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።

እናም በዚህ ሁኔታ ላይ ምንም ሳንሰራ ልጆቻችንን የምናበላው በጠፋበት ጊዜ የከተማው ገቢዎች ቢሮ የንግዱ ማህበረሰብ የደረሰበትን ጉዳት ታሳቢ ሳያደርግ ከእያንዳንዱ ነጋዴ ግብር ክፈሉ ተብለን እየተጉላላን ነው፣ ቅሬታችንንም አንቀበልም ብለውናል።

ግብር መክፈል ግዴታ ቢሆንም በጦርነት ውስጥ የከረመ ሰውን ታሳቢ ሳይደረግ በዚህ ደረጃ ከምረው መጫናቸው አግባብ አይደለም፣ ድምፃችንን አሰሙልን።

Photo: File

@EliasMeseret
24.8K viewsElias M, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 19:40:42
#Update
28.3K viewsElias M, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 19:26:02
የፋና ቡንደስሊጋ እና ላሊጋ የሆነ ዘገባ!

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ትክክለኛ መግለጫ ምን ይላል? "የንጹሀን ሶማሌዎች ደም እየፈሰሰ ነው፤ የእኛ ጊዜም ይመጣል... ይቅርታ ወደ እኛ ቢመጣ እንኳን በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕዝባችን ላይ ጉዳት ያደረሱትን ፈጽሞ አንረሳውም።"

ፋና ምን ብሎ ዘገበው? "በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦብነግ መካከል የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ የሶማሌ ክልል ህዝብ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ሰላም፣ መረጋጋትና ሁለንተናዊ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል።"

ለማመሳከርያ ስክሪንሾቶቹ ተያይዘዋል። ቡንደስሊጋ እና ላሊጋ ወይም ሀራምባ እና ቆቦ የሆነ ዘገባ ማለት ይሄ ነው።

@EliasMeseret
28.2K viewsElias M, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:20:34 የሚሻለው የህዝብ ጥቆማዎችን መቀበል እና ማጣራት ማድረግ ወይስ ለማዳፈን መሞከር?

በቅርቡ በቦሌ ኤርፖርት ባሉ ብልሹ አሰራሮች ዙርያ አንዳንድ መረጃዎችን አጋርቼ ነበር፣ የተወሰኑ እርምጃዎችም እንደተወሰዱ መስማቴን እንዲሁ። በርካታ ሌሎች ግለሶችም 'እኛም ላይ እንዲህ ደርሷል' በማለት ማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃ አጋርተዋል። እኔ ያጋራሁት መረጃ ጉዳይ አየር ማረፊያውን ከሚያስተዳድሩ አካላት ጋር እንጂ ከአየር መንገዱ ጋር በቀጥታ እንደማይገናኝ ለማስረዳት ሞክሬያለሁ።

ይህንን በአራት ባለስልጣናት ዛሬ የተሰጠ መግለጫን ሳነብ መጨረሻ አካባቢ "በኤርፖርት ዙሪያ የወንጀል ተግባራት ላይ በሚሳተፉ ሰዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል" ይላል። መልካም።

ይሁንና ቅሬታው በቀጥታ በአየር መንገዱም ዙርያ ቢሆንም ጥቆማዎችን አመስግኖ ተቀብሎ ማጣራት ማድረግ ይገባል እንጂ ለማዳፈን መሞከር አይጠቅምም።

ይበልጥ የሚገርመው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወሮ ሰላማዊት ዳዊት ለኢቢሲ "የስራ ጫና በሚኖርበት ወቅት ችግር የሚፈጥሩ ሰራተኞች እንዳሉ እንገነዘባለን" ብለው ትናንት ተናግረው ነበር።

ነገር ግን ሀላፊዋ በልጁ ላይ በቅርቡ የተፈፀመ እንግልትን መረጃ ያጋራ አቶ ነብዩ ሲራክ የተባለ ግለሰብ ጋር ስልክ በመደወል "ሚዲያ ላይ መወራቱ ማንንም አይጠቅምም፣ ምናልባት እናንተን ታዋቂ popular ሊያደርጋችሁ ይችል ይሆናል፣ ተቋሙ ያለ መረጃ መሰደብ የሌለበት ተቋም ነው" እንዳሉት መረጃ አጋርቷል።

ከህዝብ የሚደርሱ ቅሬታዎች እና ጥቆማዎች ለለውጥ ለሚሰራ አካል መሻሻሎችን ለማድረግ ከፍተኛ ግብዐቶች ናቸው፣ የስም መነሳት ብቻ ለሚያሳስበው አካል ግን ትንኮሳዎች እና የስም ማጥፋት ድርጊቶች ናቸው።

Note: እዚህ መግለጫ ላይ ለተገኙ አንድ ሀላፊ በኤርፖርት ስለሚሰሩ ውንብድናዎች መረጃ ከማስረጃ ጋር በቀጥታ አድርሻቸው ነበር፣ ሊንክ ላክልኝ ብለው ከላኩላቸው በኋላ እስከዚህ መግለጫ ድረስ ዝምታን መርጠው ቆይተዋል።

*ኢቢሲ ይህን ዜና ሲያጋራ የህዝብ አስተያየት ፈርተው ይሁን ሌላ ባላውቅም ከሌሎች ዜናዎች በተለየ የአስተያየት መስጫ (comments section) ቆልፈው ነው።

@EliasMeseret
19.1K viewsElias M, edited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:20:16
18.4K viewsElias M, 10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 18:00:09
ይህ የአዲስ አበባ ፖሊስ እርምጃ መልካም ጅማሬ ነው፣ ወደፊትም ከህዝብ በሚደርሱ ጥቆማዎች ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ዳሰሳ (monitoring) የሚያደርግ ቡድን በራሱ የሰው ሀይል በማቋቋም ህዝብን የሚያጭበረብሩ ግለሰቦችን ወደ ፍትህ ሊያቀርብ ይገባል፣ እኔም በሙያዬ ለማገዝ ዝግጁ ነኝ።

በእነዚህ ካናዳ እንልካለን በሚሉ ሰዎች ዙርያ የዛሬ 15 ቀን ገደማ ቀን ይህን መረጃ አጋርቼ ነበር: https://t.me/eliasmeseret/7494

አሁንም በድፍጋሜ ለማሳሰብ: ካናዳ የሰው ሀይል ሲያስፈልጋት በመንግስት ተቋሞቿ እና አብራቸው በምትሰራቸው ኤጀንሲዎች በኩል እንጂ በደላሎች ወይም በቲክቶክ እና ቴሌግራም በሚያስተዋውቁ ግለሰቦች እንዳልሆነ የካናዳ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቆ ነበር።

የካናዳ ወኪሎችን በተመለከተ የበለጠ ለመረዳት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይከተሉ እና ራስዎን ከመጭበርበር ይጠብቁ: https://www.canada.ca/en/immigration-refugees-citizenship/services/immigration-citizenship-representative/learn-about-representatives.html

@EliasMeseret
26.0K viewsElias M, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ