Get Mystery Box with random crypto!

ከደብረ ማርቆስ ከሚደርሱኝ መረጃዎች! በከተማው በመከላከያና ፋኖ መካከል በነበረው እና አሁንም | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ከደብረ ማርቆስ ከሚደርሱኝ መረጃዎች!

በከተማው በመከላከያና ፋኖ መካከል በነበረው እና አሁንም እየቆየ በሚያገረሸው ጦርነት የንግድ ሱቆች ለበርካታ ወሮች ዝግ ነበሩ፣ ስራ መስራት አልቻሉም ነበር፣ በዛ ላይ አብዛኞቹ የንግድ ሱቆች በጥይት የተበሳሱና ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።

እናም በዚህ ሁኔታ ላይ ምንም ሳንሰራ ልጆቻችንን የምናበላው በጠፋበት ጊዜ የከተማው ገቢዎች ቢሮ የንግዱ ማህበረሰብ የደረሰበትን ጉዳት ታሳቢ ሳያደርግ ከእያንዳንዱ ነጋዴ ግብር ክፈሉ ተብለን እየተጉላላን ነው፣ ቅሬታችንንም አንቀበልም ብለውናል።

ግብር መክፈል ግዴታ ቢሆንም በጦርነት ውስጥ የከረመ ሰውን ታሳቢ ሳይደረግ በዚህ ደረጃ ከምረው መጫናቸው አግባብ አይደለም፣ ድምፃችንን አሰሙልን።

Photo: File

@EliasMeseret