Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-03-26 16:00:20 "አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ሰዎች ጭምር ናቸው"

ሁለት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነቤተሰቦቻቸው በትናንትናው እለት መገደላቸውን በስፍራው ካሉ ሰዎች እና በደብሩ ቀደም ብለው ካገለገሉ አንድ አባት የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

በዚህ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ያገለግሉ የነበሩ መሪጌታ ስምረት የተባሉ አባት ባለቤታቸውን እና ሁለት ልጆቻቸውን፣ እንዲሁም ዲያቆን ዳንኤል የተባለ አገልጋይ ከነባለቤቱ እና ሌላ አንድ ሰው ጋር በድምሩ ሰባት ሰው እንደተገደለ እነዚህ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

"አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ናቸው። ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ምሽት ሶስት ሰአት ገደማ ነው" ያሉኝ ምንጮች ከዚህ በፊትም በጥቅምት 2012 ዓ.ም ብዙ ሰዎች ተግድለው እንደነበር አስታውሰዋል።

ነፍስ ይማር።

@EliasMeseret
46.8K viewsElias M, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-24 22:13:05
ከፒያሳ ተነሺዎች የሚደርሱኝ ሆረር ታሪኮች እንደቀጠሉ ነው!

መቼም ከተማ ሳይዘምን፣ ሳይቀየር እና ሳይነካ የትም አለም ላይ አይቆይም። ዱባይ የዛሬ 30 አመት ብትታይ የዛሬውን ትሆናለች ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ነገር ግን፣

- ለልማት እና ለከተማ ለውጥ የሚነሱ ሰዎች ለምን ብዙ ግዜ 'ሰለባ' ይሆናሉ? ስንቶች ግቡበት ተብሎ የተሰጣቸውን ለማመን የሚከብድ 'ቦታ' (ቤት ለማለት አልደፍርም) በቴሌግራም ልከውልኛል፣ ታድያ እነዚህ ቤተሰቦች ህፃናትን እና አቅመ ደካሞችን ይዘው ውሀ፣ መብራት፣ ሽንት ቤት፣ መንገድ... ወዘተ ያለሌበት ቦታ እንዴት ይኑሩ?

- ተነሱ ሲባል በሳምንታት፣ ካለም በወር ውስጥ ለምን ይሆናል? ቢያንስ ስራም ሆነ ኑሮ ማመቻቸት የሚችል ፋታ እንዲያገኝ ለምን ግዜ አይሰጥም? ጥድፊያው እና እሽቅድድሙ ከምን እና ከማን ጋር ነው? የከተማ ልማቱ፣ እድገቱ እና ማማሩ ለማን ነው? ለህዝብ ከሆነ ህዝብን ያማከለ ለምን አይሆንም?

በዚህ ዙርያ አቶ ሙሼ ሰሙ ባሰፈሩት አንድ ፅሁፍ ይህን ብለዋል፣

- በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ከ200 ሺህ ያላነሱ ነባር ይዞታዎችና ሱቆች እንደሚፈርሱ ይገመታል። ይህ ማለት ከነባር ባለ ይዞታዎቹና ከተከራይ ባለሱቆች ጋር መስተጋብር ፈጥረው የሚሰሩ ደላሎች፣ ጥበቃዎች፣ ጽዳት ሰራተኞች፣ ተቀጣሪ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሰጭዎች ሲደምሩበት ቁጥራቸው ከ500 ሺህ ሊበልጥ ይችላል። ቤተሰቦቻቸውንና ጥገኞቻቸውን ስናክልበት ደግሞ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሊሆኑ ይችላሉ።

ግድ የለም... ሰው፣ ሰውነት እና ሰብአዊነት ከየትኛውም ልማት ይቀድማል።

ፎቶ: የጥንቷ ፒያሳ

@EliasMeseret
17.0K viewsElias M, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-24 20:09:15 የትዊተር (ኤክስ) አካውንት እንዳለኝ ለጠየቃችሁ፣ ይህ 181,000 ተከታታይ ያለው አካውንቴን መቀላቀል ትችላላችሁ: https://x.com/EliasMeseret?s=09

መልካም ሰንበት።
24.9K viewsElias M, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 22:47:31
ይህን ኮሚክ አሁን ገና ማየቴ ነው...!

ማስለቀቂያ ብር እንደተከፈለ ያለው ማረጋገጫስ ምን ይሁን?

እንደው ህዝቡን እንዴት ብታስቡት ነው?

@EliasMeseret
39.8K viewsElias M, edited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 20:32:43
ለስራ ከቤታቸው ወጥተው ለበርካታ ቀናት ተይዘው የቆዩት እነዚህ ወገኖች ተለቀው አዲስ አበባ መድረሳቸው ተሰምቷል

ትላንት ማምሻውን እንደተለቀቁ እና በሠላም ተጉዘው አዲስ አበባ ሲደርሱ የዞኑ ዋና አስተዳዳር አቶ ብርሃኑ ኩናሎ በስፍራው ሆነው ተቀብለዋቸዋል ብሎ ዞኑ አስታውቋል።

ወደ ስፍራው ያቀኑት ለስራ እንደነበር የሚያሳዩ ደብዳቤዎች እና መረጃዎችን ከዚህ ቀደም አጋርቼ ነበር፣ በርካቶች በወቅቱ ሊቀበሉት ባይፈልጉም።

ለማንኛውም እንኳን ነፅ ሆናችሁ።

@EliasMeseret
39.0K viewsElias M, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 02:25:24 30 ሺህ ሰው ያሳተፈው 'ብኩን' ፊልም!

ከትግራይ እስከ አማራ እና አፋር ክልሎችን አዳርሶ ቢያንስ 600,000 ሺህ ህዝብ እንዳለቀበት የሚገመተው የሰሜኑ ጦርነት ዳፋ ገና ተነግሮ እንኳን አላለቀም።

በውጊያ ወቅት ሞተው አስከሬናቸው ገና ያልተቀበሩ በርካቶች አሉ፣ የአካል ጉዳተኞች ዊልቼር ሳያገኙ መሬት ለመሬት እየዳሁ እያየን ነው፣ የተደፈሩ ሴቶች ስነ ልቦና ገና አልተጠገነም፣ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚደረገው እንቅስቃሴ ገና ከመሬት አልተነሳም፣ የሰላም ስምምነቱን ማፅናት ላይ እንኳን ከሰሞኑ እንደሰማነው ውይይት ገና እየተደረገ ነው።

በዚህ ሁሉ መሀል በታንክ፣ ጀት፣ መድፍ፣ ክላሽ እና RPG የታገዘ በጭካኔ የተገዳደልንበትን ፊልም በ30 ሺህ ህዝብ አጅቦ የሚተርክ ፊልም በተለይ አሁን ባለንበት ወቅት ምን ሊጠቅመን ነው?

ዳግም ግጭት የመቀስቀስ ሙከራ ወይስ ሌላ? በዚህ ፊልም እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም... ወዘተ ለዘላለም ያጡ ወገኖች አሟሟታቸውን በፊልሙን ቢመለከቱ ምን ይሰማቸዋል?

ከማውቃቸው ሰዎች ተደጋግሞ እንደሰማሁት የፊልሙ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ፊልሙ በብዙ መቶ ሚልዮን ብሮች እንደወጣበት፣ በመንግስት በኩል የቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ድጋፍ ተደርጎለት እንጂ ተጨማሪ ብዙ መቶ ሚልዮን ብሮች ሊያስወጣ የሚችል ፊልም እንደሆነ ተናግሯል።

ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ወደ አሜሪካ ፊልሙን ለትርዒት ይዞ በሄደበት ወቅት "ፊልሙን እዚህ አሜሪካ ተቃውመው የሚንከባለሉ ሰዎች ይኖራሉ" ሲል እንደነበር በስፍራው የነበሩ ሰዎች አጫውተውኛል።

ጊዜውን ያልጠበቀ 'ብኩን' የሆነ የ image ግንባታ ፊልም ብዬዋለሁ። Timing የሚባል ነገር ወሳኝ ነው።

@EliasMeseret
43.2K viewsElias M, 23:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-23 02:25:14
40.8K viewsElias M, 23:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-20 01:10:12
#FactCheck ማምሻውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ሥር  መዋላቸውን አስታውቋል።

የመንግስት ሚድያዎች ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ፎቶ ጋር የተለያዩ የጦር መሳርያዎች ፎቶዎችን አብረው አያይዘው አውጥተዋል።

ሁለቱ ምስሎችን reverse image search በማድረግ ለማጣራት ስሞክር የቆዩ ምስሎች መሆናቸውን ለመመልከት ችያለው።

አንደኛው ፎቶ የዛሬ ስምንት አመት የቱርክ የፀጥታ ሀይሎች የፍተሻ ቦታ ተደብቆ ያገኙት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የዛሬ ሁለት አመት በራሳቸው የሀገራችን የመንግስት ሚድያዎች ከአይኤስ የሽብር ቡድን ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሳርያዎች እንደሆኑ ተደርጎ ቀርቦ ነበር።

የሁለቱም ቆየት ያሉ ምስሎች ውጤት ተያይዟል።

@EliasMeseret
25.3K viewsElias M, 22:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-19 18:54:19
እውቁ የሰርጀሪ ህክምና ባለሙያ ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ እሁድ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ የጠዋት ሩጫ በማድረግ ላይ ሳሉ ግድያ እንደተፈፀመባቸው ታውቋል።

ዝርዝር መረጃውን ከፖሊስ እንጠብቃለን።

ነፍስ ይማር፣ ዶክተር።

@EliasMeseret
37.5K viewsElias M, edited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-19 02:53:41
ምን እያለን ነው?

በሚሰራበት ተቋምም ሆነ በግሉ የህዝብን ብሶት እና ችግር ለአመታት ትንፍሽ ሳይል ቆይቶ አሁን ደግሞ ችግሩ ታምኖበት ባለ ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ወደዚህ የሰነዘረው ትችት የፈሪ ዱላ ሆነብኝ።

የዛሬ ስድስት እና ሰባት አመት ከነበረው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ እና እንቅስቃሴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሀገር ውስጥ ባሉ ጉዳዮች ላይ በሚፅፉ በተለይ የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ላይ "አርፋችሁ ተቀመጡ" ማስፈራርያ በማድረስ የሚታወቀው ይህ ሰው...

ከንግድ ባንክ የሚበልጥ ፎቅ ከሚያሰራው GTNA ሚድያ እስከ ባለሀብቶች 'እየደወለብን'' ቅሬታ ብዙ ማለት ይቻላል። ሰከን ማለት ሳይሻል አይቀርም፣ ከግል ጥቅም የህዝብ ድምፅ ይቀድማል።

@EliasMeseret
37.9K viewsElias M, edited  23:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ